ያቀናነው ገበያ — እዩት ተሽመድምዶ ሻጩ ሲያረፋፍድ — ገዢ መጣ ማልዶ በመደብ ስንጠብቅ — በየቋንቋው ለምዶ * * * ገበያችን ደራ — ሻጭ ተትረፈረፈ ገዥ በነቂስ ወጣ ፣ ደጋግመው ሲገዙን —ደጋግመው ሲሸጡን በተሸጥን ቁጥር ዋጋ ብናወጣ ። * * *ማንበብ ይቀጥሉ…
እምዬ ያልታደለች
እምዬ ያልታደለች ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች እምዬ ሰከረች ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች! የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋትማንበብ ይቀጥሉ…
እውነትን ፍለጋ
እኔ እኔ ከገንፎ ውስጥ ስንጥር ስጠረጥር ስንጥር ውስጥ አገኘሁ ገንፎን ያህል ሚስጥር ሽንፈቴን ልቀበል ስህተቴን ገጠምኩኝ ካንቺ ጋር ስጣላ ከራሴ ታረ‘ኩኝ አንቺ ከተኩላ መንጋ ውስጥ በግ ስለተመኘሽ ከበጎችሽ መሀል ተኩላሽን አገኘሽ እውነትሽን ስትሸሺ ግራ ስለገባሽ ከራስሽ ተፋተሽ ከባዳ ተጋባሽ ያገባሽው ባዳማንበብ ይቀጥሉ…
ሕዝባዊ ከያኒው
ሕዝባዊ ገጣምያን፣ እነዚያ ሬዲዮ ጣቢያ የሌላቸው፣ ግጥም ማንበብያ መድረክ ያልተዘረጋላቸው፣ ግጥሞቻቸው የሚያሳትሙበት ጋዜጣም ሆነ ሌላ ሚዲያ ያልተመቻቸላቸው እነዚያ አዝማሪያንና አልቃሾች ነገሥታቱን ብቻ ሳይሆን፣ በሕብረተሰቡ ውስጥ ልሂቅና ጉልህ የተባለውን ሁሉ ይተቻሉ። ቃሉን ያጠፈውን፣ በሕዝብ ላይ የቀለደውን ይገስፃሉ። ንጉሥ ሣህለሥላሴ ንጉሥ ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ትብልዬ
የማያልፉት የለም ፣ ያ ሁሉ ታለፈ ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣ ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ🙄(ርዕሱ አይደለም😂) ።። መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየትማንበብ ይቀጥሉ…
“ኑ ሀገር እንስፋ!”
ክፍፍል መችነበር፥ በአምላክ አሰራር ፥በቅድመ አፈጣጠር ሰው ሰው ብቻ ነበር ፥ዘሩ ሳይቆጠር። ሰውነት ተንዶ፥ እንዲህ እንደዛሬ ፥ ሳይኖር መበታተን የመቆጣጠር ዛር ፥ መቃብር ሳይከተን አንድ እናት ነበረን ፥ ቀሚሷ እንደኪዳን ፥ ሁላችን ምንለብሰው ዛሬ ተለያይተን፥ ክብሯን እንደ እቃቃ ፥ ዳቦማንበብ ይቀጥሉ…
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ
የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ። እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ። አሰታወሰኝ አስታወሰኝ። ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀውማንበብ ይቀጥሉ…
ሁሉም ለምን ያልፋል?
የጣፈንታ መዳፍ ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ “ሁሉም ያልፋል ” ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ? ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር ደሰታሽማንበብ ይቀጥሉ…
ጐጆ ቤት
ሀገርስ ጐጆ ናት !!! መሪዋም ምሰሶ ሹማምንቷም ማገር አንዳንዶቹም ቋሚ ሌሎቹም ወጋግራ ሰራዊቷም አጥር! ሀገርስ ጐጆ ናት !!! ሕዝቡም ክዳን ሆኖ ጐጆውን አልብሶ እንደሳር ቢቀጥን፤ ቢኖር ተራ መስሎ ከዝናብ ያድናል፤ ውርጩን አሰናብቶ ፀሃይን ይከላል፤ በጥላው ከልሎ… ሀገርስ ጐጆ ናት !!!ማንበብ ይቀጥሉ…
በኅዳር ውስጥ እኔን
(የነፍሴ ክስ) ተወው! ቆሻሻህን ተወው ከሳቱ ዳር እራቅ ጭለማን ልበሰው ጥቁር ካባ ደርብ ዓይንህ ይጨልመው። … ግዴለህም ተወው እቤትህ ግባና ዓይንህን ጨፍነህ ስላሳመምካቸው ስላቆሰልካቸው ነፍሳት አስብና ራስህን ክሰስ ራስህን ውቀስ ራስህን አጥን ተረማመድበት በንፁሀን ፋና። … የነፍስህን እድፍ የውስጥህን ጉድፍማንበብ ይቀጥሉ…