ኖረሽ እይው በቃ

(ለoptimistቶች) ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ ዘልለሽ አትጠግቢ ስቀሽ አትሰለቺ ወርሃ- ፅጌ ነው አመት ሙሉ ላንቺ። ደሞ በየቀኑ ፋሲካ ነው ኑሮሽ ያለም ሰቀቀኑ ሩቅ ነው ለጆሮሽ (የፍጥረት ሰቆቃ) ለጋ ነው አእምሮሽ ገላሽም ነው ጮርቃ ሌላም አልልሽም ኖረሽ እይው በቃ። በየጎዳናሽማንበብ ይቀጥሉ…

ወንዞች

በሕይወት መንገድ ላይ አሉ ብዙ ወንዞች ምንሻገራቸው  ወንዙ ፈተና ነው ፈተናው ፈተና አሉት እልፍ ጭንቆች። ስንቶች ተሻገሩ፤ ስንቶች ተወሰዱ ስንቶቹ ሰመጡ ይኼ ነው ጥያቄው ይኸው ነው ሚዛኑ ይኸው ነው ልኬቱ ሰው ከተፈጠረ ሙት እስኪባል ድረስ አፈር እስኪገባ አሉት ብዙ ወንዞችማንበብ ይቀጥሉ…

እኔ እምፈልገው

እውነት ለመናገር፥እኔ እምፈልገው ካንቺ ጋር መጋባት ይህን ሐምሌ ፊቴን፥ ደጋግሞ ማራባት ከወፎች ጋር መንቃት፥ በጊዜ ቤት መግባት “ምንም ድሀ ቢሆን፥ ባይኖረውም ሀብት ከደጃፍ ሲቀመጥ፥ ደስ ይላል አባት” ለሚል መናኛ ጥቅስ ፥ ኑሮየን ማይመጥን ሲሻኝ በየባንኩ፥ ስፈልግ በሳጥን የተረፈኝ ገንዘብ ደጃፍማንበብ ይቀጥሉ…

የባከነ ሌሊት!

  ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ። ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱማንበብ ይቀጥሉ…

አይደለም ምኞቴ

አይደለም ምኞቴ ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም እይደለም ምኞቴ ከንፈርሽን ማለብ ቀሚስሽን መግለብ ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ ደረትሽን ማለም ጡትሽን መሳለም በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም አላማየ አይደለም:: ምኞቴን ልንገርሽ? ካለሺበት ቦታ: ቀልቤንማንበብ ይቀጥሉ…

ተፈጥሮን ደጅ ልጥና

” እኔ ልሙትልሽ” እያልኩኝ አልምልም ቃላቴን መንዝሬ: ለሞት ቀብድ አልከፍልም ያኔ ትዝ ይልሻል? “ራስህን ግደል” ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ እድሜ ለስጦታሽ: ታጠበ ሸሚዜ። ገደብ ጫፍ በሌለው: በልቤ መጋዘን ቢታጨቅ መከራ: ቢጠራቀም ሀዘን “ባለፈልኝ” እንጂ “በሞትኩ” ብየ አላቅም ካልጋ ላይ ነውማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያዊ ነን!

ፈቅደን ሲመሩን፤ ችቦ ተቀባይ ለሚነዱን ግን ፤ አሻፈረን ባይ ካልነኩን በቀር፤ ቀድመን ማንዘምት ከጋሻ በፊት ፤ ጦር የማንሸምት ኢትዮጵያዊ ነን! ህብር ያስጌጠው፤ ህይወት ለማብቀል ዘር ሳናጣራ ፤ የምንዳቀል ለነዱን ሰይጣን፤ ለመሩን ሰናይ ጌታን ከገባር፤ ለይተን ምናይ፤ ኢትዮጵያዊ ነን! ብዙ ህልሞችን፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ስንት ጊዜ ሆናችሁ?

መሃል አዲስአባ…ሸገር ላይ እያላችሁ.. የእንቁራሪቶች ድምፅ በደንብ ከሰማችሁ በክር የታሰረ ጢንዚዛ ካያችሁ የማርያም ፈረስን መንገድ ካገኛችሁ በእፉዬ ገላ ‹‹ያዘኝ አትያዘኝ›› ከተጃጃላችሁ… ስንት ጊዜ ሆናችሁ? ሱዚ የሚዘሉ ፔፕሲ የሚራገጡ ሸክላ እየፈጩ በርበሬ ነው የሚሉ ሙሽራ ሙሽራ – እቃ እቃ እቃ እቃማንበብ ይቀጥሉ…

እያንዳንድሽ!

ወገን! ግጥሙ በሁዋላ ይደርሳል፤ ይሄ አጭር ማሳሰቢያ ነው! እያንዳንድሽ! ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ ፤ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በፀደይ ወቅት፤ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ ፤የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ፤አጎጠጎጤሽን በውሃ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፤ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ፤ በሽቦማንበብ ይቀጥሉ…

ያመት በአል ማግስት ትእይንቶች!!

– የተመጠጠ ቤት የሞላ ሽንትቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!! -ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!! -የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት-ወለምማንበብ ይቀጥሉ…