ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ዘጠኝ)

ከሁሉም ከሁሉም ምኑ ያስጠላል መሰለሽ? ራስሽን ባልሽ ካባለጋት ሴት ጋር ማነፃፀር …… መድቀቅ የምትጀምሪው እዚህጋ ነው …… ራስሽን ከሆነ ሰው ጋር ማነፃፀር ስትጀምሪ በራስ መተማመንሽ እየተምዘገዘገ ይፈጠፈጣል። ከዛ በፊት ከማንም በልጣለሁ ወይም ከማንም አንሳለሁ ብዬ ራሴን ከማንም አወዳድሬ አላውቅም እራሴንማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ስምንት)

‘ጊቢ ግቡ’ እስኪባል ድረስ ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ማንም FBE በLAW እንደማይቀይረኝ እያወቅኩ ሞከርኩ። ላለመማርም አስቤያለሁ። ከዛ ልጄን ይዤ የሆነ ቦታ እልም ብዬ መጥፋት ……. ማንም የማያውቀኝ ቦታ ሄጄ ከዜሮ መጀመር። በእኔ እልህ ልጄን ማስከፈል የማይታሰብ ነው። እጅ መስጠትምማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ሰባት)

ይሄ ሁሉ ሲሆን በጌታ ነን በጌታ ፍቅር ጥላ ስር ሆነን ነው የምንፋቀረውም የምንቧቀሰውም። ቸርች እናስመልካለን። የምሬን የምፀልይለትስ “ጌታ ሆይ ቁጣውን እንዲገታ እርዳው” ብዬ እሱ በተቃራኒው “ጌታ ሆይ ዱላዬን የምትችልበት ፀጋ ስጣት!” እያለ እየፀለየ ይሁን እንጃ አይደለም ተመትቼ ጮክ አድርገው ተናግረውኝማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኩ ነው (ክፍል ስድስት)

ሳፈቅር ገገማ ነኝ!! ግግም ያልኩ ሰገጥ!! የተመታሁት እኔ …… ቢላ አንገቴ ላይ የተደረገው እኔው …… እሱ ለሰራው ጥፋት ማስተባበያ የምሰጠውም እኔው ……. ሁለቱንም ጊዜ እኔ ስቆጣ ነው ሌላ ሰው የሆነው ስለዚህ እኔ እሱ ሲቆጣ ባልፈው ያኛው እሱ አይመጣም ብዬ አሰብኩ!(ሰገጥማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል አምስት)

“ማሚ” ከማለቴ እናቴ በስልኩ እልልታዋን አቀለጠችው። ፀሎት አይሉት ወሬ “ጌታ ሆይ ምን ይሳንሃል? ጸሎቴን ሰማኸኝ እልልልልል …… ልጄ? ደህና ነሽ?” “ደህና ነኝ!” እያልኳት እሪታዬን እለቀዋለሁ “ምን ሆነሽ ነው? የት ነው ያለሽው ?አሁኑኑ ልምጣ ?” “ምንም አልሆንኩም! ናፍቃችሁኝ ነው።” ስለእሱ ላወራትማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል አራት)

 በሚንቀጠቀጡ እጆቼ ደመነፍሴን ቢላ አንገቴ ላይ ያደረገ እጁን ለቀም አድርጌ ያዝኩት። ያዝኩት እንጂ እንዲያሸሽልኝ ልገፋው ወይ ራሴን ላሸሽ አቅሙ አልነበረኝም። የአቅሜ ጥግ ሳጌ ድምፁ እንዳይሰማ አፍኜ እንባዬን ማዝነብ ብቻ ነበር። እጁ አንገቴ ላይ ቢላዋ መደገኑን እጆቼ ሲይዙት ገና ያወቀ ይመስልማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል ሶስት)

 ሁለተኛውን ባሌን እስክተዋወቀው ሰዓት ድረስ ዓለሜ ሁሉ እሱ ነበር (የመጀመሪያው ባሌ) ትምህርቴ …. ትዳሬ …. ፍቅሬ …. ቤተሰቤ … ጓደኛዬ …. ወንድሜ ……. ይሄን ሁሉ ከኋላዬ ትቼ እርሱን መርጫለሁኛ!! እንዲህ ነበር የሆነው «ይዘኸኝ ጥፋ!» ያልኩት ቀን ከተማ ይዞኝ ሄዶ ቀለበትማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል ሁለት)

የሳመኝ ቀን “በናትህ ይሄን ነገር በምስክር ፊት አድርግልኝ” ብለው ደስ ባለኝ። ስሜ መራራ ነዋ። ሳመችው እንጂ ሳማት አይባልልኝማ! እርግጥ የሳመኝ እለት ያልኳችሁ ቀን ማለት በዋዛ የተገኘ እንዳይመስላችሁ “ጌታ ሆይ ይሄ ሰው በወንድምነት ይሁን በባልነት ፍቅር የሚወደኝ መለየት የምችልበት ፀጋ ስጠኝ!ማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!!

ግርምታችሁን እና እርግማናችሁን ከማዥጎድጎዳችሁ በፊት ትንፋሽ እየሰበሰባችሁ ከመጀመሪያው ልጀምርላችሁና ሁለቱንም ላስተዋውቃችሁ። የመጀመሪያው ባሌ “ባለቤቴ ነው ተዋወቂው!” ብዬ ያስተዋወቅኳት ጓደኛዬ “ወየው በፈጣሪ ባልሽ ሲያምር አጣብሺኝ!” ያለችለት ውብ ነው። የገዛ እናቴ ልክ እንደጠበስኩት ስታውቅ “ውይ ልጄ የልጁን ህይወት አታበልሺ አጉል ታደርጊዋለሽ !ይቅርብሽማንበብ ይቀጥሉ…

ከነጋሪት ጉሰማ፤ወደ ጉማ

ኢትዮጵያ ዘመም ስትልና ስትቃና የኖረች አገር ናት፤ በነዋሪዎቿ መካከል ያለው አንድነት ባንዱ ዘመን ይታመማል፤ በሌላው ዘመን ይታከማል። ዛሬ ጋብ ባለ ጦርነት እና መልኩ ባልታወቀ መጭ ዘመን መሀል ቆመናል፤ ተደባበረናል፤ ተጠማምደናል ፤ “ እንገንጠል” “ ይገንጠሉ “ የሚሉ የቃላት ልውውጦች አየሩንማንበብ ይቀጥሉ…