የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ነበር የተማሪዎቼ የንድፍ ስራ በሙሉ አረንጓዴ…ቢጫ…ቀይ መሆን የጀመረው። የሆነ የቪላ ንድፍ ከመስራታቸው በፊት ሀሳባቸውን በቅርፃ ቅርፅ እንዲያስረዱ ቀለል ያለ ስራ እንሰጣቸዋለን። ያው ያኔ የነበረው መንፈስ ከእጩ አርክቴክትነታቸው በልጦባቸው ቢሮ ውስጥ የሚከመረው ነገር በሙሉ አንድ አይነት ሆኖማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን ወደ ፊት
ከምናምን አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለሥላሴ እና በጎጃሙ ገዥ ራስ ሃይሉ መሀል ሃይለኛ የስልጣን ትግል ይካሄድ ነበር ፤ ራስ ሃይሉ ከብዝበዛና ከውርስ የተገኘ መአት ብር ነበረው ፤ ተፈሪ ከጎጄው ጋር ሲወዳደር እልም ያለ ችስታ ነበር ማለት ይቻላል ፤ በዚያ ላይ ተፌማንበብ ይቀጥሉ…
ድሎት እየዘሩ
ይቅርብኝ ፍሪዳው፥ አልጠግብ- ባይ ይብላው ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው ግዴለም ይለፈኝ ! ጊዜ ምቾት ነስቶ ምንጣፉን አንስቶ ፤ ፅናቱን ያውሰኝ በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤ መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ:: አውቃለሁ አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም ድሎት እየዘሩ ፥ ድልማንበብ ይቀጥሉ…
ንጉሥ መሆን 2
እንደ ካሊጉላ ዓይነት መንፈስ ላለው ንጉሥ መሆን ሥራው አልያም: ደግሞ የ’ለት እንጀራው ማለት ነው። ግና ንጉሥ መሆን ያልፋል ይራመዳል ከዕለት እንጀራነት ንጉሥ መሆን ያልፋል ከስም ማሥጠርያነት ይልቅ ያሥፈልጋል አብነት ሊያደርጉት የዘርዓ ያዕቆብን ቆራጡን ልብ ኣይነት ፍት’ እንዳይሣሣት በልጅ ላይ ጨክኖማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ሥነ ፅሁፍ’ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ፤ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጥናታዊ ፅሑፉ ጨመቅ (Summary) ለንባብ እንዲመች ተደርጎ እንደሚከተለው ቀርቧል።ማንበብ ይቀጥሉ…
“መንገድ ተዳዳሪ ነኝ
“መንገድ ተዳዳሪ ነኝ። ‘መተዳደር’ ከባድ ቃል ነው። ‘መተዳደር’ የሚለው ቃል በሐምሌ ብርድ ወፍራም ጋቢ ተከናንቦ አጃ መጠጣት ይመስላል። ግን እንዴት ነው መንገድ ላይ እየኖሩ መተዳደር? . . . ላውንቸር ተሸክሜ በኩራት የተራመድኩበት ጎዳና ላይ፤ ሀገር እንደሌለው ሰው አፈር ‘እፍ’ ብዬማንበብ ይቀጥሉ…
ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (ዳሰሳ)
“የኢትዮጵያ ምድር አንቺ የደም ጎዳና መስክሪ አፍ አውጪና” (ምኒልክ ወስናቸው) “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”፤ አዳም ረታ በአብዮቱ ዘመን የነበሩ የአንድ ሰፈር ልጆችን ሕይወትና ዕጣ ፈንታ የሚያሳይበት ትረካ ነው። አዳም፤ የእነዚህን ልጆች እድገትና ጉርምስና፣ የፖለቲካ ንቃትና አሳዛኝ ፍፃሜ በሰባት መንገዶች ወግማንበብ ይቀጥሉ…
‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ
‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ። ተረቱን ያመጣሁት፤ ደንባራ የሆነ የባዕድ ባህል ቅጂ ምን ቦታ እንደሚከተን ሳስብ እያለሁ፤ ‘ሙሾ አውራጆች የኋላ ቀር ባህል እሴቶች እንደሆኑ’ ሊነግረን የሚጥር፣ በምርምር ያልተደገፈ፣ ጥልቅ በሆነ ፍልስፍና ሞትን፣ ሃዘንና ኪነትን እንድንረዳ ለደቂቃ እንኳን ያልጣረ፣ ለስሙ ‘ለኪነ ጥበብማንበብ ይቀጥሉ…
ሽልማቱ
በቀደም ሰይፉ ላይ የሰማሁት ዜና እንዲህ ይላል ”የናይጀርያ ዜግነት ያላቸው ሌቦች አዲሳባ ገብተዋል” 🙂ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋራ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆን አለበት! ሌብነት ሲነሳ የሚከተሉት አስተካዥ ገጠመኞች ትዝ ይሉኛል፤ ሰውየው የበግ ነጋዴ ናቸው፤ ወደ ገበያ ሲሄዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ እንደተለመደው አንድማንበብ ይቀጥሉ…
ክትባት እንዴት እንዳመለጠኝ
አበሻ ገራሚ ህብረተሰብ ነው! ማስክ ገድግደህ ሲያይህ” ይሄን ያህል ትንቦቀቦቃለህ እንዴ” እያለ ያሸማቅቅሀል ፤ ከዚያ አጅሬው አስተኝቶ ለሳምንታት ያክል አበራይቶ ትቶት ይሄዳል፤ ከዚያ እንዴት ነህ? ስትለው” በዝሆን እግሩ ረግጦ አድቅቆ ለቀቀኝ በማለት ፈንታ” ይዞ ለቀቀኝ “ በማለት አቃሎ ይነግርሃል፤ ከህመሙማንበብ ይቀጥሉ…