እንደሱ አይደለም

የምወዳቸውን ዘፈኖች ወደ ሙዚቃ ቪድዮ መቀየራቸውን ስሰማ ለማየት ፈራ ተባ እላለሁ ፤ በጣም የወደድኩትን ዘፈን በካሜራ አጉል ተርጉመው ሲያበላሹብኝ ይነደኛል ፤ በራሴም ደርሶብኛል ፤ ከጥቂት አመታት በፊት ነፍሱን ይማርና ኤልያስ መልካ አንድ ዜማ ሰደደልኝ፤ “ ዝምታየ” የሚል ግጥም አለበስኩና መልሼማንበብ ይቀጥሉ…

ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ሦስት)

“ልጅ ልሰጥሽ ስለማልችል ትተይኛለሽ?” አለኝ “ስንጋባም መውለድ እንደማትችል ታውቅ ነበር?” “አዎ ” “ለምን አልነገርከኝም?” “እንዳላጣሽ ፈርቼ። ብነግርሽ ኖሮ ታገቢኝ ነበር?” “ምርጫ አልሰጠኸኝምኮ! ከልጄና ከፍቅርህ እንድመርጥ ምርጫ አልሰጠኸኝም! ራስህን ራስህ መረጥክልኝ!! ” “እኔ ብሆን ልጅ አልሰጠሽኝም ብዬ አልተውሽም! ይሄን የሚሻገር ፍቅርማንበብ ይቀጥሉ…

ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ሁለት)

ሰይጣን ይሁን ራሴ ወይም ፈጣሪ ለሀጥያት በቀጠሩልኝ ቀን ከአለቃዬ ጋር ባለግኩ። ይኸው ነው ሀጥያቴ! ጨው የሌለው አልጫ ወጥ አልጫ ወጥ የሚል ትዳር ውስጥ ፀጥ ለጥ ብዬ እንድቆይ ባለእዳ ያደረገኝ ሀጥያቴ ይኸው ነው!! ይኸው ነው ብዬ አቀለልኩት? ካልጠፋ ቀን የዛን ቀንማንበብ ይቀጥሉ…

ቅጥቅጥ! በላባ ትራስ!

ብልፅግና ፓርቲን ለመደገፍ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲወገዝ አይቸ ገረመኝ ! ብልጥግናን እንደግፋለን ዳንኤል ክብረትን እናወግዛለን ማለትኮ “ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንሞታለን በረኛውን ግን እንገድለዋለን “ እንደማለት ነው ፤ ዳኒ አንደበቱ የማይደነቃቀፍ ተናጋሪ ብእሩም የማይደክም ፀሀፊ ነው፤ማንበብ ይቀጥሉ…

ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!! (ክፍል አንድ)

“ቦታችን በተለመደው ሰዓት እጠብቅሃለሁ። አፈቅርሃለሁ!” የሚል መልዕክት ነው እንዲህ ያስቦረቀኝ!! እሱ ጏዳ ቁርስ እያበሰለ የሚያማስለው የመጥበሻ ድምፅ ይሰማኛል። ስልኩ መልእክት ሲቀበል ድምፅ አሰማ ያለወትሮዬ እጅ ጥሎኝ ስልኩን አነሳሁት። አንደኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው! እኔና እሱ የኛ የምንለው ቦታ ኖሮን አያውቅም!! ከቤታችንማንበብ ይቀጥሉ…

ወይዘንድሮ

ወይ ዘንድሮ- አለ ስንዝሮ- አንድ ዶላር በአምሳ ሁለት ብር ዘርዝሮ ! እንደማመመጥ! የተሻለ ይመጣል ብለን ስንጠብቅ፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት አዲስ የኮቪድ ጎረምሳ ፈቶ ለቆብናል ፤ በአምናውና በዘንድሮው ኮቪድ መካከል ያለው ልዩነት ምን ብየ ላስረዳችሁ? በልዩሃይል እና በሪፓብሊካን ጋርድ መካከል ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

ታሪክን የሁዋሊት

በዘመነ የጁ በ1837 ዓም ግብፆች በገዳሪፍ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው ገብተው ነበር፤ በጊዜው የደምቢያ ገዥ በነበሩት ደጃዝማች ክንፉ የተመራ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪዎችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጅቱዋል ፤ እንጦኒዮስ ደአባዲ የተባለ መንገደኛ መዝግቦ ያስቀመጠው የጥንት ግጥም ስለጦርነቱ የሚከተለውን ይተርካል፤ ‘የረጀባ ተዝካርማንበብ ይቀጥሉ…

በእሾህ መንገድ መሀል

ያገሩ አየር ጠባይ ቆላ- ወይን- አደጋ ከላይ የሚያስፈራ፥ ከታች የሚያሰጋ አጉል ነው መንገዱ ቅፅሩም ሲገዝፍ ያድራል፥ በቁመት በወርዱ እና ምን ይጠበስ? የማይቆም ጅረት ነኝ፤ የማይቀለበስ ቢገፏት፥ ቢያዳፏት ከቅርንጫፏ ጋር የማትነጣጠል በወጀብ መሀከል ፥የምትደንስ ቅጠል እንደዚህ ነኝ እኔ፤ ምቾትስ ለምኔ ቀይማንበብ ይቀጥሉ…

አሜሪካን ፀሀይና የአገሬን ሚድያ ያመነ

“ስሙኝ ልንገራችሁ ታሪኬን ባጭሩ” አለ አለማየሁ እሼቴ የሆነ ጊዜ ! ከዛ ረዘም አድርጎ ዘፈነ። ስሙኝ ! ትናንት በቤቴ መስኮት መስታወት አሻግሬ ወደ ውጭ ስመለከተ ፀሀይ በሰላሳ ጥሩሷ ፉዋ ብላለች! እሰይ ! Thank you Global warming አልኩ! ወደ ባህር ዳርቻው ወጣማንበብ ይቀጥሉ…

አብደአመቱ

እንሆ በጎርጉራውያን ዘመን አቆጣጠር 2021 ገባ! በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ግን ገና 2013 ነው ፤ እንዲህ አይነት ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ከሁለቱ የካሌንደር ቀማሪዎች አንዱ ሂሳብ ይፎርፍ እንደነበር በመገመት እንለፈው፤ ዘመን መለወጫ ድሮ ቀረ ! ማለቴ ኢትዮጵያ ቀረ! እኔ ጋ ያለ በረዶማንበብ ይቀጥሉ…