ግጥሎት

ቀጥሎ የምታነቡት ነገር በግጥምና በፀሎት ማሃል ያለ ነገር ነው። ግጥሎት ብየዋለሁ😉ትናንት በእንቅልፍና በንቃት ማሃል ሆኘ የመጣልኝ ነው። ወፍ እንዳገሩዋ ትጮሃለች! ነፍስ እንደዘመኑዋ ትፀልያለች! የፅሁፌ አላማ ራሴን እና ብጤዎቼን ለማዝናናት ብቻ እንደሆነ ይታወቅ! አባት ሆይ ! እንሆ ዛሬ ተወለድሁ! ካለመኖር ወደማንበብ ይቀጥሉ…

አፍረን ቀሎ እና የአቡበከር ሙሳ ገድል (ክፍል ሁለት)

የአቡበከር ሙሳ የኪነ-ጥበብ ስጦታ በጣም ይደንቃል። ራሱን በአንዱ የጥበብ ዘውግ ሳያጥር ሁሉንም ያዳርሳል። በአንድ ወቅት ዓሊ ቢራ ቃለ-ምልልስ ሲደረግለት “ፊሎሶፈር ነበር” ብሏል። አቡበከር ከጻፋቸው ዘመን አይሽሬ ድርሰቶች መካከል ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን እንጥቀስላችሁ። ሐሚዶ መሐመድ ድሬ ዳዋ ካፈራቻቸው የአፍረን ቀሎ ቡድንማንበብ ይቀጥሉ…

አፍረን ቀሎ እና የአቡበከር ሙሳ ገድል

ዛሬ የኢንተርኔቱ ወሬ ስለ ዓሊ ቢራ ሆኗል። ዓሊ አልሞተም። ዛሬም በሙሉ ጤናው ነው ያለው። ነገር ግን ዓሊን ኮትኩቶ ያሳደገው የጥበብ መምህሩ ልክ የዛሬ አርባ ዓመት ሞቶ ነበር። በዚህ ጽሑፍ የዚያን የጥበብ ገበሬ ስራዎች እንቃኛለን። —— ዓሊ ቢራ በአማርኛ አንድ ዘፈንማንበብ ይቀጥሉ…

አባይ እና ጣና- በጀምስ ብሩስ ካርታ ላይ

ጀምስ ብሩስ ይህንን ካርታ ያነሳው በ1770ዎቹ ነው። ፈረንጆች እርሱ የጻፈውን መጽሐፍ አንብበው “ጀምስ ብሩስ የጥቁር አባይን ምንጭ አገኘ” ይላሉ። ጳውሎስ ኞኞ በዚህ ዙሪያ ሲጽፍ “አረ ለመሆኑ ዕድሜ ልኩን ከአባይ ጋር ሲኖር የነበረው የጎንደርና የጎጃም ገበሬ የት ሄዶ ነው ፈረንጆች እንዲህማንበብ ይቀጥሉ…

የኤርትራ ህልም (ክፍል ሁለት)

የኢትኖግራፊ ሽርሽራችን በኤርትራ ምድር ቀጥሏል። አሁን ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት ቆላማ አውራጃዎች እዚህ ነው ያሉት። አቆርዳት፣ ተሰነይ፣ አሊጊደር፣ ኡምሐጀር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞች በቆላው ምድር ውስጥ ተዘርግተዋል። ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ የሚባሉት ብሄረሰቦች እዚህ ነው የሚኖሩት። የአካባቢው ዋነኛውማንበብ ይቀጥሉ…

እኔና አንቺ

“አንተ ሴሰኛ አይደለህም።” ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን። ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት። ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገንማንበብ ይቀጥሉ…

የኤርትራ ህልም!

ኤርትራ ድሮ የኛው አካል ነበረች። አጼ ኃይለ ሥላሤ ለሁላችንም አስፈላጊ የነበረውን የፌዴሬሽን ፎርሙላ ሰረዙትና ህዝቡን አስቀየሙት። ደርግ ደግሞ የራሳችንን ህዝብ እንደ ባዕድ እየቆጠረ በመትረየስ አጨደው። በታንክ ደመሰሰው። በዚህም የተነሳ ወጣቱ “አደይ ኤሪቲሪያ”ን እየዘመረ ወደ ባርካና ሳህል ነጎደ። ራሱን አደራጅቶ ጀብሃናማንበብ ይቀጥሉ…

የገቢዎች ነገር እና 40/60

በጥዋት አልጋዬ ውስጥ ሆኜ እየተብሰከሰኩ ነው። የቤት ኪራይ መክፈያዬ ደርሷል……ኤዲያ! ” መቼ ነው ግን የራሴ ቤት የሚኖረኝ?” ።ትላንት በጉጉት ስጠብቀው የነበረው የ40/60 እጣ እንደወጣ በዜና አይቻለሁ…እጣ ውስጥ የተካተቱት መጀመሪያውኑም መቶ ፐርሰንት የከፈሉ ብቻ እንደሆነም ተነግሯል……የወጣው እጣ አንድ ሺ እንኳን አይሞላም።ማንበብ ይቀጥሉ…

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ

(ታሪካዊ ልቦለድ) To be honest with you ሲያትል በተደረገው የዲያስፖራ የግርኳስ ውድድር ወደ ሚደረበት ስቴዲየም የሄድኩት ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳልነካካ መፅሃፌን ሸጬ አገሬ ለመግባት ነበር፤ (ከመፅሃፍ ሻጭ የሚገኘው ገቢ አስር በመቶ ለእኔ ሲሆን ፤ ቀሪው ለቤት አከራየ ለጋሽ ጣሰውማንበብ ይቀጥሉ…