ጋሹ እንዴት እንደተሰደደ?

  የዚች ጨዋታ መነሻ የሆነኝ የዛሬ ምናምን አመት ያነብኩት “ያረብ ሌሊቶች ” ተረት ነው። ጋሹ ታታሪና አይናፋር ባላገር ነው። ሲኖር ሲኖር; በስንት መከራ አንዲት ቆንጆ አጭቶ አገባ። የሰርጉ ቀን ተበልቶ ተጠጥቶ ጭፈራው ደራ። ሚዜዎችና አጃቢዎች ሙሽሮች እንዲጨፍሩ ጋበዙዋቸው። ጋሹ ግብዣውንማንበብ ይቀጥሉ…

ራስ አሉላ አባ ነጋ – የኢትዮጵያ ጀግና!!

በዘመነ አብዮቱ (ደርግ) በትግራይ ክፍለ ሀገር ፣ ዓድዋ አውራጃ ፣ አባ ገሪማ ገዳም ከወትሮው የዝምታ እና የመናንያት የተመስጦ ቀናት ውጪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብና የጦር ሰራዊት ገዳሙ ተርመስምሷል። የገዳሙ መናንያንም በከፍተኛ የድግስ ዝግጅት ተጠምደዋል። በቦታው በአካል ከነበሩ ሰዎች መሀል የልጅነትማንበብ ይቀጥሉ…

ኢትዮጵያ በአማልክት እና በተከታዮቻቸው ዓይን

“… እናቴ ሆይ በዚህች በምባርካት አገር በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችን እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ አሥራት ይሆኑሽ ዘንድ ሰጥቼሻለሁ። እናቴ ሆይ አሁንም ወደዚያች አገር እንሄድ ዘንድ ተነሺ። ደሴቶችና የተቀደሱ፣ ወንዞችዋ ያማሩ፣ ውሃዎችዋ የጠሩ፣ ዛፎችዋና ተራራዎችዋ የተዋቡ ናቸውና አሳይሻለሁ አለኝ።” ይላል አንብር መስቀልየማንበብ ይቀጥሉ…

እርዳታ እና እኔ

ግኑኝነታችን የሚጀምረው፣ በልጅነቴ ከበላሁት የእርዳታ “ፋፋ” እና “ዘይት” ነው። የሆነ ጊዜ ወተትም ነበር። የሆድ በሽታ ለቀቀብኝና ለሳምንታት ላይና ታይ በሌ ስል ኖሬ ይቺን ዓለም በጨቅላነት ሳልገላገላት ለትንሽ አመለጥኩ። ኑሮን በድህነት ስትገፋ በወር የሚሰጥህ 5 እና 10 ኪሎግራም ምጽወታ ነፍስህን ለማቆየትማንበብ ይቀጥሉ…

እትት በረደኝ

“ጅላዋት ሆይ፣ ጮማ ክፋት ከመጣ ሰላሳ እግዜር፣ ሰላሳ አላህ አይመልሰውም።” “….በዲሞክራሲ ስለማምን አይደለም። ምንድን ነው እሱ? ልግመኛ ቢሰበሰብ የአንዲት ጮጮ ክዳን አይከፍትም። ፍትህ ፍትህ ፍትህ የምትባለዋም የነብር ቂንጥር ናት። በሥዕል ይህቺ ፍትህ የሚሏት ሴትዮ ቆማ አይቼአታለሁ፤ ሚዛንና ሰይፍ ይዛ። ሰይፉማንበብ ይቀጥሉ…

የጎረቤት ወግ

  ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት ከጨዋ ሚኒ ማርኬት ሁለት ኪሎ ማንጎ ገዛሁ፤ “በጥቁር ፌስታል አርጊልኝ” አልኩዋት ማሾን(ማሾ የሚኒ ማርኬቱ ባለቤት ናት) “አንተ ደሞ የጥቁር ፌስታል ልክፍት አለብህ “አለችኝ እየሳቀች። ውነቷን ነው! ከፍራፍሬው ጥራት በማይተናነስ መጠን የፌስታሉ ቀለም ያሳስበኛል፤ ጥቁር ፌስታል በውስጡማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አላቅሱኝ››

ትላንት አባቴ ሞተ። ካሁን በኋላ በለመድናት ሰአት የውጪ በራችንን በቁልፉ ‹‹ቃ›› አድርጎ ከፍቶ ላይገባ፣ ካሁን በኋላ ሳመሽ በረንዳ ላይ ጋቢውን ለብሶ እሳት ጎርሶ ጠብቆ ላይቆጣኝ፣ ካሁን በኋላ የአመት በአል ድፎ እየሳቀ ላይቆርስ፣ ካሁን በኋላ ልጄን፣ የልጅ ልጁን አቅፎ ላይስም… ሞተ።ማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የሪል እስቴት ማላገጫዎች››

አሁንስ እነዚህ ኑሮ እጅ በጆሮ ያስያዘው ምስኪን ሕዝብ ላይ በይፋ የሚያላግጡ የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች ቃር ሆኑብኝ። አነፈሩኝ። መቼስ፣ በለስ ቀንቶት፣ ወርሶ ወይም ከመንግሥቱ ነዋይ ግርግር ጀምሮ ቆጥቦ እዚህ ለደረሰ የናጠጠ ሃብታም ማስተዋወቃቸውን አልቃወምም። እነዚህ በሌላ የተንጣለለ እልፍኛቸው እየኖሩ ማስታወቂያውን የሚመለከቱማንበብ ይቀጥሉ…

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስልከኞች የስራ ደንብ

አጤ ምኒልክ የመጀመሪያውን ስልክ አገልግሎት ላይ ካዋሉ በኋላ የተወሰኑ መኳንንት እና አጤ ምኒልክ ስራቸውን በስልክ አማካኝነት ማከናወን ችለው ነበር። ሆኖም ግን የስልክ ግንኙነቱ የሚቀላጠፈው በስልከኞች አማካኝነት ነበር። ብዙውን ጊዜ ስልከኞቹ ከስልኩ ቤት እየጠፉ ችግር ስለፈጠሩ አጤ ምኒልክ የሚከተለውን የስልከኞችን የተራማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ተዘጋጂ፤ ግን አትሂጂ››

ይህች መናጢ ግብፅ ከኤርትራ ጋር ተሞዳሙዳ፤ ‹‹አንድ ቀን ታርቀን ቤት ሰርተንበት በአብርሃም አፈወርቂ እና በቴዲ አፍሮ ዘፈን አብረን እንጨፍርበታለን›› ያልነው ዳህላክ ላይ የጦር ቤቷን መገንባት ጀመረች አይደል? ግብፅም፣ አዲሷም ተኝተውልን አያውቁምና ነገሩ ብዙ ባይደንቅም ክፉኛ ያስተክዘኝ ገብቷል። የሚያምሰን ነገር በዝቶማንበብ ይቀጥሉ…