የዘጠኝ አመቷን የጓደኛዬን ልጅ የአማርኛ ምሳሌያዊ ንግግር ላስተምር እየታተርኩ ነው። ሶስተኛው ላይ ነን። መፅሃፉ ላይ በተርታ ካሉት ውስጥ ለሷ የሚመጥነውን መርጬ አንብቢ አልኳት። ‹‹ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም›› ጮክ ብላ አነበበች። ‹‹ጎበዝ! ምን ማለት ይመስልሻል?›› ‹‹እ….እ….›› አለች እያንጋጠጠች። ‹‹ቀስ ብለሽማንበብ ይቀጥሉ…
የአራዊት ጥበቃ ታሪክ በኢትዮጵያ
በእንግሊዝ አገር የአራዊት፣ የአእዋፍና የአሳ መጠበቂያ ማህበር ግንቦት ፲፪ (12) ቀን ፲፰፻፺፫ (1893) ዓ/ ም መቇቇሙንና ኢትዮጵያም በዚህ ማህበር እንድትገባ በማለት ሙሴ ቤርድ ለምኒልክ ኣጫወታቸው። የደምቡንም ግልባጭ አነበበላቸው። ምኒልክ በሰሙት በአራዊት ጥበቃው ደንብ ተደሰቱ። ይህንንም ሁኔታ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ መንግስት ባለሙሉማንበብ ይቀጥሉ…
ቅርንጫፉ እንደ ዛፉ
የጋምቤላ ክልል የትምህርት ቢሮን ጨምሮ ዘጠኝ የክልሉ ‹‹ስራ አስፈፃሚዎች›› በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሰበብ ተከስሰው መባረራቸውን ሰማን። በእውነቱ፤ በዚህ ዜና የሚገባውን ያህል ልደነግጥ ባለመቻሌ አዝኛለሁ። በስንቱ ልደንግጥ…? በተለይ በትምህርት ጉዳይ መደንገጥ ያቆምኩት፤ በዛ ዘሞን መንግስት እድሜ ጠገቡን ትምህርት ቤት ‹‹ለልማት›› ማፍረሱንማንበብ ይቀጥሉ…
ሸምበቆ እና ሸንኮሬ
አመት ከማይሞላው ጊዜ በፊት ለመስክ ስራ ወጣ ስል እግረ መንገዴን ‹‹የአባቴን ሀገር እና ዘመዶች ልይ›› ብዬ ከተወለደበት የገጠር መንደር ጎራ ብዬ ነበር። በቅጡ ያልወጠንኩት የእግረ መንገድ ጉዞዬ ወሬ አባቴ ዘመዶች ዘንድ ከብርሃን ፈጥኖ ደረሰና እኔን ለማስተናገድ ወጥነው ሲንገላቱብኝ ሰነበቱ። በተለይማንበብ ይቀጥሉ…
ለሊዮ ቶሎይስቶይ የተጻፈ ደብዳቤ
(እውነተኛ የሰሙኑ ገጠመኝ) አንድ ወዳጄ ከሳምንታት በፊት አንድ ቴአትር ይጽፍና በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ቴአትር ቤቶች ወደ አንዱ ይሄዳል፡፡ ድርሰቱን ለግምገማ እንዲያስገባ ይነገረዋል፡፡ አስገባ፡፡ በቀደም ዕለት የግምገማውን ውጤት ለማየት ወደ ቤተ ተውኔቱ ያመራል፡፡ መዝገብ ቤቶቹም ‹የግምገማው ውጤት ደርሷል፡፡ መታወቂያዎትን አሳይተውማንበብ ይቀጥሉ…
ተአምረ መኪና
(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ ) ወደ ረከቦት ጎዳና የሚወስደኝን አውቶብስ እየጠበቅሁ ነው። አውቶብሱ ከመድረሱ በፊት ከ’ፋኖቼ አንዱ በዚህ ካለፈ ሊፍት ይሰጠኛል ብየ ተስፋ አረግሁ። ፌርማታው፣ በጎዳና አዳሪዎች ሽንት ጨቅይቷል። እና የቆምኩበት ቦታ ለfan ሳይሆን ለጉንfan የተጋለጠ መሆኑ ገባኝ። ዙርያ ገባውን ስመለከት፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ገነት ይቅርብኝ
“እንለያይ?” ስላት አስቀድማ ውብ ከንፈሮቿን ገለጥ አድርጋ የሲኦል መቀመቅ ውስጥ ሰምጬ እንኳን ቢሆን ንዳዱን የሚያዘነጋኝን ጥርሶቿን አሳየችኝ። ቀጥሎ ግን የእውነቴን መሆኑን ስታውቅ ሳሳዝናት ደፍሬ ማየት የሚከብደኝ ውብ ዓይኗ ደፈራረሰ። “ማለት?” አለችኝ በተሰበረ እና የአፏን በር ለቆ ለመውጣት በሚቅለሰለስ ድምፅ “እንድንለያይማንበብ ይቀጥሉ…
“የፖለቲካ ትልቁ ጥቅም ሽፋን መስጠቱ ነው”
ታውቃላችሁ ፖለቲከኞቻችን ትልልቅ ነገር እየተናገሩ ይማርኩናል። ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቲቪ አስደግፈው ያማልሉናል። አንድ ዛፍ ይተክሉና ስለዚህ ስለተከሉት ዛፍ አስር ሰአት ያወራሉ። ይሄን የሚሰሙ የዋሃን እና ቂሎች፣ ዛፍ ብቻ ሳይሆን በቃ ደን ያደገ ይመስላቸዋል። ድርጊቱ ደቃቃ ቢሆንም ከጥዝጠዛው ብዛት የእውነት ትልቅ ይመስላቸዋል።ማንበብ ይቀጥሉ…
ከአሸናፊዎች መዳፍ ወደ የተሸናፊዎች ወገብ
‹ሰላም ከተሸናፊዎች ወገብ እንጂ ከአሸናፊዎች መዳፍ አትገኝም› የሚል ወርቃማ አባባል አላቸው የካናዳ ጥንታውያን ሕዝቦች (First Nations)። አደን ልዩ ችሎታቸው የነበረውና በዚህች ሀገር ከሺ ዓመታት በፊት ሠፍረው መኖር የጀመሩት እነዚህ ሕዝቦች አያሌ የእርስ በርስ ጦርነቶችንና ችግሮችን ለመፍታት የቻሉት በዚህ ምክንያት እንደነበረማንበብ ይቀጥሉ…
የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር
የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው። ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል። ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱትማንበብ ይቀጥሉ…