ቀለማቱን በተመለከተ . . .

‹‹የስንብት ቀለማት ውስጥ ያሉትን ቀለማት በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብም ቀደም ሲል ራሴም እንደማሳሰቢያ ለማስቀመጥ በልቦናዬ የሻትኩት ነጥብ ነው። በጥልቅ ሂስ ስራ ወይም እዛም ባይደርስ በተራ ግምገማ ድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሱት ቀለማት ምን ማለት ናቸው? ምን ይወክላሉ? ብሎ ጥያቄ ማንሳት ትክክል ነው። በአጭሩማንበብ ይቀጥሉ…

ገንዘብ መሆን የተሳነው እውቀት

ከታናሽ ወንድሜ ጋር በዲግሪ ፕሮግራም ተምሮ የተመረቀውን ዳንኤል የኮብልስቶን ስራን ሲያስተባብር አግኘሁት። ሻይ ይዘን ስለ የተማሩ ኮብልስቶን ጠራቢ እና ደርዳሪዎች ተብሎ ተብሎ የተተወውን ክርክር እንደ አዲስ አደረግን። ዳንኤል ‹‹ ስራ አጥተን ቤት ቁጭ ከምንል ገንዘብ እስካገኘን ብንሰራ ምናለ?›› ብሎ ነገሩንማንበብ ይቀጥሉ…

የባል ገበያ – (የመጨረሻ ክፍል)

“ጌትዬ ንረገኝ? ያሰብሽው ልክ አይደለም በለኝ?” ከየት መጣ ያላልኩት እንባዬ ከቃላቱ ጋር ፈሰሰ። አይኖቼን ሽሽት ፊቱን አዙሮ ዝም አለኝ።…… “ኦ…ህ ማ…ይ ዲ…ር ጋ…ድ! አዲሱ(የመውደድ አባት ነው) ያወራልኝ ልጅ እንዳትሆን?” መውደድን ነው የምትጠይቀው ቀጠል አድርጋ “አባቷ ሊሞት ነገር ነው ካልተሳሳትኩ?” እሱንማንበብ ይቀጥሉ…

ያስራ ሦስት ወር ወሬ

ፈረንጆች ያልተገደበ የንግግር ነጻነት አላቸው። ምን ዋጋ አለው ታድያ፤ በፈረንጅ አገር ሰው ርስበርሱ አይነጋገርም። ኒዮርክ ወይም ሎንዶን ውስጥ ባቡር ተሣፈር። ምድረ ፈረንጅ ምላሱን ቤቱ ጥሎት የመጣ ይመስል እንደተለጎመ ተሳፍሮ እንደተለጎመ ይወርዳል። ልታወራው ስታቆበቁብ ፊቱን እንደ ቪኖ ጠርሙስ በጋዜጣ ውስጥ ይሸፍናል።ማንበብ ይቀጥሉ…

የባል ገበያ – (ክፍል አራት)

“እመኚኝ እኔን ነው እየጠበቅሽ ያለሽው።…… ” እንዳምነው ያወራናቸውን ሁሉ ነገሮች አንድ በአንድ ያወራንበትን ወር፣ ቀንና ሰዓት ሳይቀር ሲነግረኝ…… አንድ የሆነ የተዛባ ነገር የተፈጠረ መሰለኝ…… አይኔ አልያም ጆሮዬ ካልሆነም ህልም ነው…… መውደድ? አይሆንም!! አይሆንም!! …… “መውደድ እየቀለድኩ ነው በለኝ?” “እየቀለድኩ አለመሆኔንማንበብ ይቀጥሉ…

ፍቅፋቂ

“ዝም! ጭጭ! ጩሐት አይደለም ብትተነፍሺ በዚህ ጩቤ ነው የምዘለዝልሽ!” ብሎ አስፈራርቶኝ ነው እዚህ ሜዳ ላይ ያጋደመኝ። በዚህ ውርጭ፣ በዚህ ጨለማ፣ ሰው ዝር በማይልበት ጥግ ልብሴን ገፎ ቆዳዬን ከአፈር እያነካካ፣ አጥንቴን ከድንጋይ እያማታ የሚያደርገኝን የሚያደርገኝ በጩቤ አስፈራርቶ ነው። “ስጋሽን እዘለዝለዋለሁ” አለ?ማንበብ ይቀጥሉ…

“ከፋይ ገበሬ ነው”

(‹‹ከፋይ ገበሬ ነው›› ከገጣሚ ሞገስ ሐብቱ አንዲት ግጥም በውሰት የመጣች ሰንኝ ናት) ‹‹ኢትዮጵያ የአሜሪካን ህግ በጣሰ እና ባልተፈቀደ የአባይ ቦንድ ሽያጭ ምክንያት ከ6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለአሜሪካ መንግስት ልትከፍል ነው። ›› የሚለውን ዜና ሰማን። የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በሚገኘው ኤምባሲውማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ቢልልኝ››

(መታሰቢያነቱ፡ ‹‹ለምወድሽ››) ….ዛሬስ ልቤ ወጌሻ የሚፈልግ ይመስለኛል፣ የኔ ጌታ። ልቤን የሚያሽ ወጌሻ ፈልግልኝ እስቲ..ስብራቱን የሚያቃና። ‹‹አስራ አራት አመት ካልወለዳችሁ ከዚህ ወዲህ የመውለድ እድላችሁ ዜሮ ነው›› ነው ያለው ሀኪማችን? ከዚያ ሁሉ ምርመራ፣ ከዚያ ሁሉ ምልልስ፣ ከዚያ ሁሉ ተስፋ በኋላ፤ ‹‹አስራ አራትማንበብ ይቀጥሉ…