ሠርገኛ መጥቶም በርበሬ ቀንጣሽ ጠፋ

ስንቱ መከረኛ ወገኔ ዛሬም ፤ ‹‹አዬ ክፉ ዘመን ይቅር አይነሳ፣ አርጉዝ ላሜን ሸጥኳት- ለሁለት ቀን ምሳ›› እያለ አጣዳፊ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሲገልፅ፤ ‹‹ድርቁን ረሃብ ከመሆኑ በፊት ተቆጣጥረነዋል!›› ‹‹የውጪ እርዳታ አንፈልግም!›› ሲባል ተከርሞ፤ በዚህ ሳምንት ከወራት በፊት በጓሮ በር ቤተመንግስት ይመላለሱማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል አራት)

እኔም አልገባኝም። …… ስምሪት ለምን እናቴን አስታወሰችኝ? …… ‘ስምረት ሞተች‘ የሚለው የአርሴማ ጥሪ የፈጠረብኝ ድንጋጤ እንዴት ብሽቅ ለሆነው የአሁኑ ስሜቴ ጎታች ምክኒያት ሆነ? በውል ያለየሁት ለስምሪት የተሰማኝ ስሜት በምን ስሌት ወደልጅነት ትዝታዬ አሸመጠጠኝ? አላውቅም…… ምናልባት እስከማስታውሰው ለሰው ግድ የሰጠኝ በዚህማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል ሦስተ)

እናቴ ሸርሙጣ ነበረች። …… ሀገር ያወቃት ሸርሙጣ። …… ከማን እንደወለደችኝ አታውቅም። …… ባሏ ነው የሷ ዲቃላ መሆኔን የሚነግረኝ…… እሷም ግን ‘ሂድ ከዚህ ጥፋ! ዲቃላ‘ ትለኛለች ስትሰድበኝ… … የሌላ ሰው ነውር እንደሆንኩ ሁላ አትገባኝም። …… አንዳንዴ አቅፋኝ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች። ……ማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው (ክፍል ሁለት)

እርቃኗን ለቄንጥ የተዘረረች የሚመስል አነጣጠፍ ነው ወለሉ ላይ የተነጠፈችው።…… አልፎ አልፎ የሳሙና አረፋ ሰውነቷ ላይ አለ። ከፊል ፀጉሯ ወለሉ ላይ ተበትኗል። …… ከፊሉ በትከሻዋ አልፎ ደረቷንና የግራ ጡቷን ሸፍኖታል። (ፀጉሯን ሁሌም ጠቅልላ ነው የማውቃት… … ረዥም ፀጉር እንዳላት አስቤ አላውቅም)ማንበብ ይቀጥሉ…

አለመታደል ነው ቀላውጦ ማስመለስ

“ከኔና ከሱስ ምረጥ” ስትለኝ ቀኑ ቅዳሜ ነበር። …… ስልኬን ጆሮዬ ላይ እንደለጠፍኩ ዙሪያዬን ቃኘሁት። …… በሱሶቼ ተከብቢያለሁ።(ያሟላሁ ሱሰኛ ነኝ።) “መቼ?” አልኳት “አሁኑኑ!” “ዛሬ ከሆነ ሱሴን ነገ ከሆነ ግን አንቺን!” መለስኩላት። ዘጋችው። …… መልሳ እንደማትደውል አውቃለሁ። …… ጥፋተኛው ማነው? ራሷን ከቅጠልማንበብ ይቀጥሉ…

ጅንጀናው

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ዲሲ ውስጥ ፈረንጆችና አበሾች የሚያዘወትሩት ሬስቶራንት አለ። ካጠገቡ የሶማልያ ሬስቶራንት ተከፍቷል። ኢትዮጵያ ሲፈርድባት አሜሪካ ውስጥ እንኳ ከሶማሌ ጋር ተጎራብታለች። ክፍሉ ውስጥ የተለያዩ ፊቶች ይታዩኛል ። ጭው ያለ ፊት – ከእንቅልፍ ጋር የተቆራረጠ ፊት – እናቱን የናፈቀ ፊት-ዶላርማንበብ ይቀጥሉ…

“ጊዜ ቤት” ጊዜ ያልተወሰደበት ፊልም

ከሰሞኑ ያላየኋቸውን የአማርኛ ፊልሞች ለማየት ዓለም ሲኒማ ጎራ አልኩኝ። …… እግር እና እድል ጥሎኝ “ጊዜ ቤት” የሚል ፊልም ላይ ተጣድኩ። በእውነቱ ከሆነ በጓደለ እየሞላሁም ቢሆን ፊልሞቻችንን ‘ተበራቱ‘ የማለት ችግር የለብኝም። ይህኛው ፊልም ግን ቢብስብኝ ልፅፈው ወደድኩ። ማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ቢሳካማንበብ ይቀጥሉ…

መለስ ዜናዊን በጨረፍታ

በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1/1947 በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ ነው። የልደት ስማቸው “ለገሠ ዜናዊ” ነበር። “መለስ” በሚለው ስም መጠራት የጀመሩት በሚያዚያ ወር 1967 ገደማ ለትግል ወደ ደደቢት በረሃ ከወጡ በኋላ ነው። በወቅቱማንበብ ይቀጥሉ…

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው። እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ። አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበታትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማኅበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም። ሀገር ማለት ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

እምቢ እሺ አይደለም…እሺ ብቻ ነው እሺ

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከጓደኞቼ አንዱ የሚያሰቅቅ ነገር ላከልኝ። አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ በመቶ የሚቆጠሩ ወንድም ሴትም ተማሪዎችን ያሳተፈ ጥናት ውጤት ነው። ጥናቱ ስለ አስገድዶ መድፈር ነው። የመጠይቁ ብቸኛ ጥያቄ ይሄ ነው፤ ‹‹አስገድዶ መድፈር ተቀባይነት ሊኖረውማንበብ ይቀጥሉ…