ያገሩ አየር ጠባይ
ቆላ- ወይን- አደጋ
ከላይ የሚያስፈራ፥ ከታች የሚያሰጋ
አጉል ነው መንገዱ
ቅፅሩም ሲገዝፍ ያድራል፥ በቁመት በወርዱ
እና ምን ይጠበስ?
የማይቆም ጅረት ነኝ፤ የማይቀለበስ
ቢገፏት፥
ቢያዳፏት
ከቅርንጫፏ ጋር የማትነጣጠል
በወጀብ መሀከል ፥የምትደንስ ቅጠል
እንደዚህ ነኝ እኔ፤
ምቾትስ ለምኔ
ቀይ ምንጣፍ አያምረኝ
ይመስገን ዘመኔ
በእሾህ መንገድ መሀል፤ መጉዋዝ ላስተማረኝ