ቀጭን ወገቧ ላይ ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል የወርቅ መስቀሏ ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል መንገድ ላይ ያየኋት የማላውቃት ሴት ናት። ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ ሠባት እንቁላሎች ግማሽ ኪሎ ሥጋ … (ገዝቶ) ከርሷ ጋር ካልሆነ ቡና አልጠጣምማንበብ ይቀጥሉ…
“ውጪ…ልን!”
የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ነበር የተማሪዎቼ የንድፍ ስራ በሙሉ አረንጓዴ…ቢጫ…ቀይ መሆን የጀመረው። የሆነ የቪላ ንድፍ ከመስራታቸው በፊት ሀሳባቸውን በቅርፃ ቅርፅ እንዲያስረዱ ቀለል ያለ ስራ እንሰጣቸዋለን። ያው ያኔ የነበረው መንፈስ ከእጩ አርክቴክትነታቸው በልጦባቸው ቢሮ ውስጥ የሚከመረው ነገር በሙሉ አንድ አይነት ሆኖማንበብ ይቀጥሉ…
ታሪክን ወደ ፊት
ከምናምን አመታት በፊት በቀዳማዊ ሀይለሥላሴ እና በጎጃሙ ገዥ ራስ ሃይሉ መሀል ሃይለኛ የስልጣን ትግል ይካሄድ ነበር ፤ ራስ ሃይሉ ከብዝበዛና ከውርስ የተገኘ መአት ብር ነበረው ፤ ተፈሪ ከጎጄው ጋር ሲወዳደር እልም ያለ ችስታ ነበር ማለት ይቻላል ፤ በዚያ ላይ ተፌማንበብ ይቀጥሉ…
ንጉሥ መሆን 2
እንደ ካሊጉላ ዓይነት መንፈስ ላለው ንጉሥ መሆን ሥራው አልያም: ደግሞ የ’ለት እንጀራው ማለት ነው። ግና ንጉሥ መሆን ያልፋል ይራመዳል ከዕለት እንጀራነት ንጉሥ መሆን ያልፋል ከስም ማሥጠርያነት ይልቅ ያሥፈልጋል አብነት ሊያደርጉት የዘርዓ ያዕቆብን ቆራጡን ልብ ኣይነት ፍት’ እንዳይሣሣት በልጅ ላይ ጨክኖማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ሥነ ፅሁፍ’ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ፤ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጥናታዊ ፅሑፉ ጨመቅ (Summary) ለንባብ እንዲመች ተደርጎ እንደሚከተለው ቀርቧል።ማንበብ ይቀጥሉ…
ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (ዳሰሳ)
“የኢትዮጵያ ምድር አንቺ የደም ጎዳና መስክሪ አፍ አውጪና” (ምኒልክ ወስናቸው) “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”፤ አዳም ረታ በአብዮቱ ዘመን የነበሩ የአንድ ሰፈር ልጆችን ሕይወትና ዕጣ ፈንታ የሚያሳይበት ትረካ ነው። አዳም፤ የእነዚህን ልጆች እድገትና ጉርምስና፣ የፖለቲካ ንቃትና አሳዛኝ ፍፃሜ በሰባት መንገዶች ወግማንበብ ይቀጥሉ…
‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ
‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ። ተረቱን ያመጣሁት፤ ደንባራ የሆነ የባዕድ ባህል ቅጂ ምን ቦታ እንደሚከተን ሳስብ እያለሁ፤ ‘ሙሾ አውራጆች የኋላ ቀር ባህል እሴቶች እንደሆኑ’ ሊነግረን የሚጥር፣ በምርምር ያልተደገፈ፣ ጥልቅ በሆነ ፍልስፍና ሞትን፣ ሃዘንና ኪነትን እንድንረዳ ለደቂቃ እንኳን ያልጣረ፣ ለስሙ ‘ለኪነ ጥበብማንበብ ይቀጥሉ…
ስለትግራይ ሲነሳ ብዙ ይነሳል
እኔ ጭሮ አዳሪ ስለሆንኩ መጀመርያ የማስታውሰው የፅሁፍ ሰዎችን ነው፤ አለቃ ተወልደ መድህን ፤ ደብተራ ፍስሀ ወልደጊዮርጊስ ፥ ገብረህይወት ባይከዳኝ ፤ ስብሀትለአብ ገብረእግዚአብሄር ፥ ከትግራይ ምድር የተሰጡኝ የኢትዮጵያ ገፀበረከቶች ናቸው። ከ ሶስት መቶ አመት በፊት የተፃፈ የታሪክ ድርሳን አግኝተህ ብታነብ ትግራይማንበብ ይቀጥሉ…
‘The past is a foreign country’ (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው)
ይሄን የእንግሊዝኛ ተረት በዚህ ዓመት ውስጥ ሺህ ጊዜ ሳልሰማው አልቀርም። ግን መደጋገሙ ሲበዛብኝ፤ አባባሉ እንዲወደድ ስልት ያለው የማለማመጃ ዘመቻ ወጣቱ ላይ እየተሰራ መሰለኝ። ዘይቤውን የሚናገሩት ብዙ የጥቁር ሀበሻ (ሀበ) ፈረንጃዊያን ብቅ ብለዋል። እነሱም ʻየአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስʼ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተውማንበብ ይቀጥሉ…
ቅጥቅጥ! በላባ ትራስ!
ብልፅግና ፓርቲን ለመደገፍ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ወዳጄ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲወገዝ አይቸ ገረመኝ ! ብልጥግናን እንደግፋለን ዳንኤል ክብረትን እናወግዛለን ማለትኮ “ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንሞታለን በረኛውን ግን እንገድለዋለን “ እንደማለት ነው ፤ ዳኒ አንደበቱ የማይደነቃቀፍ ተናጋሪ ብእሩም የማይደክም ፀሀፊ ነው፤ማንበብ ይቀጥሉ…