ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው ፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል፥ ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም፥ ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤( አሁንማንበብ ይቀጥሉ…
ግ-ሽበት
አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ማንበብ ይቀጥሉ…
“መዶሻህን ብላው”
ወዳጄ (Netsanet) እንደነገረኝ ሰውዬው እሁድ ቀን እቤቱ ጋደም ብድግ ሲል ይቆይና ግድግዳው ላይ የተነቀለች ሚስማር አይቶ ሊመታት ቢፈልግ መዶሻ ያጣል። ጎረቤቱን ሊጠይቀው በሩጋ ከደረሰ በኋላ «ተኝቶ ቢሆንስ» ብሎ ይመለሳል። እቤቱ ከመድረሱ በፊት ግን «እህ የተኛ እንደሆነስ? መዶሻውን ከሰጠኝ በኋላ ተመልሶማንበብ ይቀጥሉ…
የጥልቁ ትንታኔ
በቀደም ስለሉሲፈር ፊልም በፃፍኩት ፅሁፍ ስር አንዱ “ትውልዱን በማር የተለወሰ መርዝ እያስነበብሽው ነው” ብሎኝ ሳቅቼ ሞተውት። እናውራ እንዴ? የትኛውን ትውልድ? ይሄ ትውልድ ቲክ ያላደረገው የሉሲፈር ስራ አለ ነው የምትሉኝ? ይሄ የኔ ዘር አይደለህም ብሎ ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው ትውልድ ሉሲፈር እሩቁማንበብ ይቀጥሉ…
ሚሽኑ
አሳዛኝ ታሪክ ትናንት በራፌ ተቆረቆረ፤ ከፈትኩ፥ ሁለት ያሜሪካ ወታደራዊ መለዮ የለበሱ ሰዎች ቆመዋል ፤ ባለባበሳቸው መገመት እንደቻልኩት አንደኛው ፊልድ ማርሻል ነው፤ ሁለተኛው ፊልድ ሻለቃ ሳይሆን አይቀርም፥ “ሚስተር ቤኪቱ” ብሎ ጠራኝ ማርሻሉ ፥ “አቤት” “እንኳን ደስ ያለህ ለብሄራዊ ውትድርና አልፈሀል! “ማንበብ ይቀጥሉ…
የባላንታይን ዋዜማ ወግ
ከብዙ ዘመናት በሁዋላ ከወዳጄ ምእዝ ጋራ ትናንት በስልክ ተገናኘን፤ ላንድ ሰአት ተኩል ያክል ስናወጋ የተረዳሁት ነገር ፤ጊዜ ብዙ እንዳልቀየረን ነው፤ “የት ልትጋብዛት ነው ያሰብከው?” ሲል ጠየቀኝ፥ “ራቅ ያለ ሰፈር ልወስዳት ነው ያሰበኩት፤ እኛ ሰፈር ያሉት ሬስቶራንቶች ሁሉ ያውቁኛል” “በሬስቶራንቶች ውስጥማንበብ ይቀጥሉ…
የሰንበት ትዝታዎች
ለመጀመርያ ጊዜ ሲኒማ የገባሁት አስራንደኛ ክፍል ሳለሁ ይመስለኛል፤ እሁድ ቀን ደብረማርቆስ ውስጥ ነው፤ ብቸኛው ሲኒማ ቤት ተከፍቶ ካስራምስት የማንበልጥ ሰዎች ታድመናል፤ ፊልሙን በቴክኒክ የሚቆጣጠረው ሰውየ የጤና እህል ማለቴ እክል ገጥሞት አልመጣም፤ ስለዚህ፥ የሲኒማ ቤቱ ዘበኛ ጋሽ ይትባረክ ሰውየውን ተክተው ለመስራትማንበብ ይቀጥሉ…
በተመን..
ከባለንጀሮቼ ጋራ ስናወራ “ እኔኮ ዲያስፖራ አይደለሁም፤ ተመላላሽ፥ ሲራራ ነኝ “ እላቸዋለሁ፤ እነሱ ግን ”እሳት ካየው ምን ለየው“ ብለው በግድ በዲያስፖራነት ይመድቡኛል፤ እሺ ለዛሬ በነሱ ሀሳብ ልስማማና ልቀጥል። ባለፈው መንግስት ዲያስፖራውን አትመጣልኝም ወይ” እያለ ሲጀነጅነው አልነበር?! ብዙ ወዳጆቼ ልባቸው በጅንጀናውማንበብ ይቀጥሉ…
ተቆርጦ የቀረው
በየነ ባልንጀራየ ነው፤ ጦርነቱ ሲጀመር “በዩማ ቲዩብ “ የሚል የዩቲዩብ አካውንት ከፍቶ መሸቀል ጀመረ፤ አንዳንዴ የድል ዜና ሲጠርርበት ሰለ አድዋ ወይም ስለዶጋሊ ድል በመተረክ ፕሮግራሙን ይሞላዋል፤ አንዳንዴ የኔን ግጥም ሳይቀር ከፌስቡኬ ላይ ወስዶ ይዶልበታል፤ ሳንቲም ማካፈሉ ይቅር ፤ ክሬዲት እንኳማንበብ ይቀጥሉ…
ዘማች
በቀደም እኔና አዩ እራት ለመብላት አበሻ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል፤ አዩ ባልንጀራየ ናት ፤ ለስድስት ወራት ያክል ብንተዋወቅም ሙሉ ስሟን አልነገረችኝም፤ ሙሉ ስሟ “ አያልነሸ” ወይም “ አያንቱ” ሊሆን ይችላል። ቅርብ ማዶ ካለው ጠረጴዛ ፊተለፊት ሁለት ፍቅረኛሞች ተቀምጠዋል፤ ሴቲቱ በሰውየውማንበብ ይቀጥሉ…