አዲሱ ዓመት በእውነት አዲስ ይሁንላችሁ! ለሁላችንም የነጻነት፣የሰላም፣ የፍቅር፣ የሥራና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን ተጠየቅ መስከረም! ተጠየቅ መስከረም፤ ዛሬስ ዋዛ የለም አንተን ለመቀበል እንቁጣጣሽ እያልን፤ ከርስ እንሞላለን፤ እንሳከራለን፤ እንጨፍራለን፡፡ አልገባኝም እኔን አንተ መወደድህ፤ ስትገባ ስትወጣ ድግስ መቀበልህ፤ ዶሮው፤ በጉ፤ ሰንጋው ይታረድልሃል፤ ርጥብማንበብ ይቀጥሉ…
ተ ላ ቀ ቅ
ከሕላዌው ጽንፍ አልባ እውነት ራስን የመነጠል ግብግብ። ከሆኑት መሆን ሌላ መሆንታን መሻት። ከአማናዊው እውነት ተናጥሎ በሃሳብ ደሴት መገለል። የኔ/ኛ፣ የእነርሱ፣ የነዚያ ባይነት ፍረጃ። ነኝነት ከሌላው የተለየ መሆንን ሲሰብክ መሆን /Being/ ቅዠት ውስጥ ይቧችራል። ነኝነት ጥግ ሲያሻትት የመሆን ቀለም ይደበዝዛል። የሆንከውንማንበብ ይቀጥሉ…
የሱፍ አበባ ነኝ
የብርሃን ጥገኛ ነኝ… እኔዬ ከብርሃን ውጭ ውበት የላትም… ብርሃን ሳጣ ይጨንቀኛል… ቅጠሎቼ ይጠነዝላሉ… ቅርንጫፎቼ ይኮሰምናሉ… የሱፍ አበባ ነኝ… በሕላዌ ገመድ ለተንጠለጠለችው ኑረት ጨለማና ብርሃን የማይዘለሉ ሃቆች ቢሆኑም እኔ ግን በብርሃን ፍቅር እንደተለከፍኩ አለሁ… ልክፍቱ “..መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ ስላልኩ የሚለቅማንበብ ይቀጥሉ…
ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም
አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ! አንዳንድ አስተሳሰቦችማንበብ ይቀጥሉ…
የመጀመሪያዋ ግብዣ
ምድርም ሰማይም ባዶ እንደነበሩ ነው ድሮ ! …እና ባዶው ምድር ላይ …እግዚአብሔር ሳር ነሽ ቅጠል ነሽ ውሃ ነሽ ፀሃይ ነሽ እንደጉድ ፈጠረው …. በግ ነሽ ዶሮ ነሽ በሬ ነሽ ዳይኖሰር ነሽ …..ፈጠረ ፈጠረና ከዳር እስከዳር አየት አድርጎ ሲያበቃ ‹‹ፓ መልካምማንበብ ይቀጥሉ…
ሸውራራ ፌሚኒዝም
ወደ ኋላ ስናይ! አባት እናቶቻችን ባለ ብዙ ስህተት ነበሩ።እንደ አብዛኛው ህዝብ።በብዙ ጉዳዮች ላይ የነፃነት አስተሳሰብን አልተከሉልንም።ትልቁ የጥሩነት መለኪያቸው፣ ለታላላቆች ቃል መገዛት፣ባህል እና ልማድን መጠበቅ ወዘተ እንጂ የልጆቻቸውን intellect በመገንባት ላይ ደካማ ነበሩ። የሚያከራክረን አይመስለኝም። ወደ ኋላ ስናይ፣ ከአሉታዊ ማህበረሰባዊ ጠባያችንማንበብ ይቀጥሉ…
ሞደ ጠባብነት፣ ከጎሳ እስከ ሀገር
«ሞደ ጠባብነት፣ ከጎሳ እስከ ሀገር… ሀንገር በጠለፋት መንደር » 😉 ፌቡም የጎጠኞች መዲና ሆናለች። ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲነፃፀር የትየለሌ ጨምሯል። ብዙ የቡድናቸው አሳቢዎች አልፎ አልፎ በመግባባት፣ ብዙ ጊዜ በመፈነካከት በዚህች መዲና ይኖራሉ። ጎሳህ ማንነት ነው የሚሉ ድምፆች ይጮሃሉ። ሎልማንበብ ይቀጥሉ…
ቀለማቱን በተመለከተ . . .
‹‹የስንብት ቀለማት ውስጥ ያሉትን ቀለማት በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብም ቀደም ሲል ራሴም እንደማሳሰቢያ ለማስቀመጥ በልቦናዬ የሻትኩት ነጥብ ነው። በጥልቅ ሂስ ስራ ወይም እዛም ባይደርስ በተራ ግምገማ ድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሱት ቀለማት ምን ማለት ናቸው? ምን ይወክላሉ? ብሎ ጥያቄ ማንሳት ትክክል ነው። በአጭሩማንበብ ይቀጥሉ…
የሰው ህሊና
ግፍና ቅሌት ያዘቦት ወግ በሆነበት በዚህ ዘመን “የሰው ህሊና” የት ገባ ብለህ ሳትጠይቅ ያደርክበት ቀን አለ? በርግጥ ህሊና የሚባል ነገር ራሱ ይኖራል? አንድን እሥረኛ ሽንት ቤት እንዳይሄድ በመከልከል የሚቀጣ የወህኒ ጠባቂ ባለበት አገር ውስጥ የህሊናን መኖር ብጠራጠር ይፈረድብኛል?በሀዲስ አለማየሁ “የልምዣት” ውስጥ ፈረደማንበብ ይቀጥሉ…
“የለ_ዓለም”
“ከዚህ ቀደም በሰው ልጅ በማንም ያልተሞከረ አዲስ ሃሳብ እና የአፃፃፍ ስልት እውን አለ?” የአጻጻፍ ቅርፅ ሃሳብ የማስተላለፊያ መንገድ ነው። የስነጽሑፍ አላባዊያን የተውጣጡት፣ ከተለያዩ ቀደምት ፀሐፍት ስራዎች ተወራራሽ መዋቅረ ውጤት (ውበት) አንፃር መሆኑም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። ይነስም ይብዛ፣ እያንዳንዱ ሰው በተመሳሳይማንበብ ይቀጥሉ…