Butterfly Effect

ተተንባይ ኑረት የሌላቸውን ሁነቶች የሚተነትነው ሒሳባዊ ንድፈ-ሃሳብ Chaos Theory ይባላል… ትወራው በዚህ ስም ከመጠራቱ በፊት መገለጫ ባሕሪያቱን ለመተንተን የመጀመሪያ ነው የሚባልለት የሒሳብ ሊቅ Henri Poincaré ይባላል… ፈረንሳዊ ነው… “It may happen that small differences in the initial conditions produce veryማንበብ ይቀጥሉ…

እግዜርን እሰሩት !!

ከስሩ ታድሞ ትውልድ ይማከራል ‹‹እናምፅ ›› እያለ ቁረጡት ያን ዝግባ ምናባቱ ቆርጦት ለህዝብ ጥላ ጣለ!? ወንበር ሊገረስስ ላገር ጣይ ሊያወጣ ጥላው ስር ተቀምጦ ህዝብ ከመከረ ዝግባ አሸባሪ ነው በግንደ ልቦናው ሳጥናኤል ያደረ ! እሰሩት !! ይጨፍጨፍ ባህር ዛፍ ምን ቅብጥማንበብ ይቀጥሉ…

ጉርሻ

‘ጉርሻ የሚያቀራርብ ነው። በጉርሻ አይኖቻችን የፈጠሩት ርቀት ይጠፋል። በኋላ እንዳየሁት መጎራረስ ወደ ወሲብ የሚጠጋ ኢትዮጵያዊ ድርጊት ነው። በማዕድ ዙርያ እንዲቀመጥ የተገደደው ተከፋፍሎ ግለሰብ የሆነው ቡድንና ማሕበረሰብ በሚዘረጋው የበላተኛ እጅ ድልድይነት ይቀራረባል። ‘አብረን በልተን’ ሲባል ውስጡ ከባድ የጉርሻ ይዘት አለ። ጉርሻማንበብ ይቀጥሉ…

ሳንሱራም!

ሳንሱራሞችን አትከልክሏቸው፣ ብትከለክሏቸውም አይከለኩልም የሚል ያልተከተበ ህግ አለ መሰለኝ።ሰዉ ሳንሱራም ነው። ያንተ ሃሳብ በገዛ ሞዱ ልክክ ብሎ ካልገጠመለት፣ ይጎመዝዘዋል። ሊያጣጥለው ላይ ታች ይወርዳል። አይዞህ ብቻህን አይደለህም፤የብዙዎቻችን ችግር ነው። የገዛ ሃሳብን እያሽሞኖሞኑ፣ የገዛ ልጅ ነው ብለው ከነንፍጡ የሚወዱ ሰዎች የሌሎች ለየትማንበብ ይቀጥሉ…

ድልድዮቹን ተውልን

እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…

Nothingness!!

መስመር መስራት ስትጀምር ወዲህና ወዲያን ትፈጥራለህ… አጥር መገንባት ስትጀምር ውስጥና ውጭ ትፈጥራለህ… ፍርድ መስጠት ስትጀምር ክፉና ደግ ትፈጥራለህ… በመስመር – አጥርና ፍርድህ ምክንያት የልዩነት ዜማ ሰርክ ይቀነቀናል… እንዲህ ‘የሆኑ’ እና እንዲያ ‘ያልሆኑ’ ክልል ይበጃል… ‘የኛ’ እና ‘የእነርሱ’ ምድብ ይሰራል። ሕይወትማንበብ ይቀጥሉ…

እኛ፣ሾፌሩና አውቶብሱ

‹ዛጎል› ልቦለድ ውስጥ የምናገኘው ዮናስ የተባለው ገጸ ባሕርይ እንደሚከተለው ያስባል፤ያምናል፤ይናገራልም! ‘በእኛ ፈቃድ አይደለም ነገሮች የሚከወኑት። እግዜራችን ነው ሾፌር። እሱ ነው ፈላጭ ቆራጭ! እሱ ነው የእኛ ሃይል። በየትኛው ጊዜ – በየትኛው ቦታ – እኛን ከመኪናው ማውረድ እንዳለበት የሚወስን። እኛ ‘ወራጅ አለ’ማንበብ ይቀጥሉ…