ግኑኝነታችን የሚጀምረው፣ በልጅነቴ ከበላሁት የእርዳታ “ፋፋ” እና “ዘይት” ነው። የሆነ ጊዜ ወተትም ነበር። የሆድ በሽታ ለቀቀብኝና ለሳምንታት ላይና ታይ በሌ ስል ኖሬ ይቺን ዓለም በጨቅላነት ሳልገላገላት ለትንሽ አመለጥኩ። ኑሮን በድህነት ስትገፋ በወር የሚሰጥህ 5 እና 10 ኪሎግራም ምጽወታ ነፍስህን ለማቆየትማንበብ ይቀጥሉ…
እትት በረደኝ
“ጅላዋት ሆይ፣ ጮማ ክፋት ከመጣ ሰላሳ እግዜር፣ ሰላሳ አላህ አይመልሰውም።” “….በዲሞክራሲ ስለማምን አይደለም። ምንድን ነው እሱ? ልግመኛ ቢሰበሰብ የአንዲት ጮጮ ክዳን አይከፍትም። ፍትህ ፍትህ ፍትህ የምትባለዋም የነብር ቂንጥር ናት። በሥዕል ይህቺ ፍትህ የሚሏት ሴትዮ ቆማ አይቼአታለሁ፤ ሚዛንና ሰይፍ ይዛ። ሰይፉማንበብ ይቀጥሉ…
የጎረቤት ወግ
ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት ከጨዋ ሚኒ ማርኬት ሁለት ኪሎ ማንጎ ገዛሁ፤ “በጥቁር ፌስታል አርጊልኝ” አልኩዋት ማሾን(ማሾ የሚኒ ማርኬቱ ባለቤት ናት) “አንተ ደሞ የጥቁር ፌስታል ልክፍት አለብህ “አለችኝ እየሳቀች። ውነቷን ነው! ከፍራፍሬው ጥራት በማይተናነስ መጠን የፌስታሉ ቀለም ያሳስበኛል፤ ጥቁር ፌስታል በውስጡማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹አላቅሱኝ››
ትላንት አባቴ ሞተ። ካሁን በኋላ በለመድናት ሰአት የውጪ በራችንን በቁልፉ ‹‹ቃ›› አድርጎ ከፍቶ ላይገባ፣ ካሁን በኋላ ሳመሽ በረንዳ ላይ ጋቢውን ለብሶ እሳት ጎርሶ ጠብቆ ላይቆጣኝ፣ ካሁን በኋላ የአመት በአል ድፎ እየሳቀ ላይቆርስ፣ ካሁን በኋላ ልጄን፣ የልጅ ልጁን አቅፎ ላይስም… ሞተ።ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹የሪል እስቴት ማላገጫዎች››
አሁንስ እነዚህ ኑሮ እጅ በጆሮ ያስያዘው ምስኪን ሕዝብ ላይ በይፋ የሚያላግጡ የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች ቃር ሆኑብኝ። አነፈሩኝ። መቼስ፣ በለስ ቀንቶት፣ ወርሶ ወይም ከመንግሥቱ ነዋይ ግርግር ጀምሮ ቆጥቦ እዚህ ለደረሰ የናጠጠ ሃብታም ማስተዋወቃቸውን አልቃወምም። እነዚህ በሌላ የተንጣለለ እልፍኛቸው እየኖሩ ማስታወቂያውን የሚመለከቱማንበብ ይቀጥሉ…
ዘውድም እነሱ ጎፈርም እነሱ
ቀምጣላ ስድስተኛ ቤቷን በአዲስ አበባ የገዛችው ዘመን ያገነነናት ሙሰኛ የድሮ የትምህርት ቤት ጓደኛዬን ካገኘሁ ወዲህ የአርባ-ስልሳ ነገር ያነደኝ፣ የኮንዶሚኒየም ኪራይ ያንጨረጭረኝ ጀምሯል። ልጅቱ አንድ ኮንዶሚኒየም፣ አንድ የሰንሻይን ሪል ሰቴት አፓርትማ፣ አንድ የፍሊንትስቶን ሆምስ ታወን ሃውስ፣ አንድ የማህበር ቤት፣ አንድ ሰበታማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ኑ! አንድ ቤት ግቡ!››
መስሪያ ቤቴ ሁለት የከፍተኛ መደብ ልጆች ብቻ የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች መሃከል የተሰነገ ነው። ጠዋት ሲገቡ፣ እረፍት ሲወጡ፣ ማታ ሲሄዱ አያቸዋለሁ። ከወዛቸው፣ ከቀብራራነታቸው፣ አማርኛን ከደቆሰው እንግሊዝኛቸው ጎልቶ የሚታየኝ፤ መጀመሪያ የሚቀበለኝ ዘወትር ዳንኪራ የሚረግጡበት አደንቋሪ፣ ተንጫራሪ ራፕ ሙዚቃቸው ነው። የነ ድሬክ፣ የነማንበብ ይቀጥሉ…
ተሰቅለን ነበር…ወረድን!
ሳምን፣በእድሜው ማምሻው መቋሚያ ይዞ፣ቅድመ ግብዓተ መሬቱን እንደሚማጠን ሰው አልነበርኩም። ቀንበጥ እድሜያችን ገፅ ላይ የተፃፈው እየሱስ ብቻ ነበር።ጌታ ሆይ ብሎ ጀምሮ፣ጌታ ሆይ ብሎ የሚቋጭ (እንዲያውም አይቋጭም ነበር)…የሚዘልቅ! ,,, መቁረቢያ እድሜው ሲደርስ፣ «የእግርህ መርገጫ የሆነችው ምድር ላይ ስትመጣ፣እኔ ላይ እርገጥ» ብሎ እንደሚንጋለልማንበብ ይቀጥሉ…
‘ጉልባን’
“… ድል አውሪ በኦፊሻል ሙያው ‘ዳቦ ጋጋሪ’ ይባል አንጂ በድብቅ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ትዝታ አንደርግራውንድ (ትን) የተባለ ድርጅት አባልና አነቃናቂ ነው። የዚህ ድርጅት ስራው ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቷ የነበሩ የኪነት ስራዎችን በፓይሬት ሬድዮ ለከተማው ህዝብ ማሰማት ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…
ሻረው፣ እንዴት እንዳመለጠ?!
ባለፈው ፣ተጠባባቂ ፓስተር ገመቹ ቸርች ካልወሰድኩህ ሞቸ እገኛለሁ አለኝ፤ “በውቄ እግዜርን ፍለጋ ላይ ነኝ ትል የለ?! ታድያ እግዜርን የምትፈልገው ረከቦት ጎዳና ዳር ቆመህ የሴቶችን ዳሌ በማወዳደር ነውን? ተው ተመከር ተው! አለም አላፊ ነው፤ መልክ ረጋፊ ነው፤”ብሎ ተከዘ። እኔም መልሼ፤”ስማ! አለምማንበብ ይቀጥሉ…