ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‘ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ሥነ ፅሁፍ’ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ፤ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎች ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል። የጥናታዊ ፅሑፉ ጨመቅ (Summary) ለንባብ እንዲመች ተደርጎ እንደሚከተለው ቀርቧል።ማንበብ ይቀጥሉ…

ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (ዳሰሳ)

“የኢትዮጵያ ምድር አንቺ የደም ጎዳና መስክሪ አፍ አውጪና” (ምኒልክ ወስናቸው) “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”፤ አዳም ረታ በአብዮቱ ዘመን የነበሩ የአንድ ሰፈር ልጆችን ሕይወትና ዕጣ ፈንታ የሚያሳይበት ትረካ ነው። አዳም፤ የእነዚህን ልጆች እድገትና ጉርምስና፣ የፖለቲካ ንቃትና አሳዛኝ ፍፃሜ በሰባት መንገዶች ወግማንበብ ይቀጥሉ…

‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ

‘እዬዬ ሲደላ ነው’ ይላሉ። ተረቱን ያመጣሁት፤ ደንባራ የሆነ የባዕድ ባህል ቅጂ ምን ቦታ እንደሚከተን ሳስብ እያለሁ፤ ‘ሙሾ አውራጆች የኋላ ቀር ባህል እሴቶች እንደሆኑ’ ሊነግረን የሚጥር፣ በምርምር ያልተደገፈ፣ ጥልቅ በሆነ ፍልስፍና ሞትን፣ ሃዘንና ኪነትን እንድንረዳ ለደቂቃ እንኳን ያልጣረ፣ ለስሙ ‘ለኪነ ጥበብማንበብ ይቀጥሉ…

ክትባት እንዴት እንዳመለጠኝ

አበሻ ገራሚ ህብረተሰብ ነው! ማስክ ገድግደህ ሲያይህ” ይሄን ያህል ትንቦቀቦቃለህ እንዴ” እያለ ያሸማቅቅሀል ፤ ከዚያ አጅሬው አስተኝቶ ለሳምንታት ያክል አበራይቶ ትቶት ይሄዳል፤ ከዚያ እንዴት ነህ? ስትለው” በዝሆን እግሩ ረግጦ አድቅቆ ለቀቀኝ በማለት ፈንታ” ይዞ ለቀቀኝ “ በማለት አቃሎ ይነግርሃል፤ ከህመሙማንበብ ይቀጥሉ…

የአባዬ መደረቢያ

ያኔ …ከዛ ከኛ ቤት ከባሰ አመዳም ደሃ ጎረቤታችን ቦቸራ ሳረግዝ…… ለአባዬ ውርደቱ ሆንኩ። በየሴሚስተሩ አንደኛ እየወጣች ስሙን የምታስጠራው ልጁ በአንድ ቀን ስህተት አፈር ከድሜ ገባች። … ወራት ነጎዱ… ትምህርቴን ከ11 ተውኩት። ልጄን ገጠር አክስቴጋ ሄጄ ወለድኩ።…… የአባዬ ውርደት የነበረው ሌባውማንበብ ይቀጥሉ…

ሞካሪና አስሞካሪ

(ማስጠንቀቂያ …. አልባሌ ነገር የማትወዱ ሰዎች አታንብቡ … ኡኡኡኡኡ .. 🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️ይሄን አልፋችሁ ካነበባችሁ እንዳትመክሩኝ) “ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።” አልኩት “እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?” “እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።” ከንፈሩን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ…… “ድንግል መሆን አልፈልግም።” አልኩት “ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም?ማንበብ ይቀጥሉ…

የቋንቋ ነገር

ለአዲሳባ ከንቲባነት ልወዳደር ወይስ ለክቡር ገና ልተውለት? ምን ያንሰኛል? ሌላው ቢቀር ሁለት ቋንቋ እችላለሁ – የአራዳና የገጠር አማርኛ አቀላጥፌ እናገራለሁ፤ የዛሬ አመት ገደማ ይመስለኛል: በካፒታል ሆቴል ጀርባ ባለው አቋራጭ መንገድ ሳልፍ ሁለት ጎረምሶች ይተናነቃሉ፤ ገባሁና ገላገልኩ፤ ሳጣራ አንዱ በቅርቡ ከታክሲማንበብ ይቀጥሉ…

እኔኮ አንጀቴን የሚበላኝ….

አሜሪካ ውስጥ በየቀኑ የማይደረግ አይነት ሰልፍ የለም! በዚህ ሁለት ሳምንት እንኳን ሁለት ሰልፍ አይቻለሁ። ኢራቃዊያን የአሜሪካን የአየር ድብደባ ተቃውመው የወጡትን ሰልፍ በመንገዴ አየሁ …የበርማን መፈንቅለመንግስት አለም ቸል ብሎታል የሚሉ በርማዊያንም ባለፈው ቅዳሜ ተሰልፈው የሆነ ዩኒቨርስቲ በር ላይ ሲጮሁ አየሁ! እዛማንበብ ይቀጥሉ…

ስለትግራይ ሲነሳ ብዙ ይነሳል

እኔ ጭሮ አዳሪ ስለሆንኩ መጀመርያ የማስታውሰው የፅሁፍ ሰዎችን ነው፤ አለቃ ተወልደ መድህን ፤ ደብተራ ፍስሀ ወልደጊዮርጊስ ፥ ገብረህይወት ባይከዳኝ ፤ ስብሀትለአብ ገብረእግዚአብሄር ፥ ከትግራይ ምድር የተሰጡኝ የኢትዮጵያ ገፀበረከቶች ናቸው። ከ ሶስት መቶ አመት በፊት የተፃፈ የታሪክ ድርሳን አግኝተህ ብታነብ ትግራይማንበብ ይቀጥሉ…

‘The past is a foreign country’ (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው)

ይሄን የእንግሊዝኛ ተረት በዚህ ዓመት ውስጥ ሺህ ጊዜ ሳልሰማው አልቀርም። ግን መደጋገሙ ሲበዛብኝ፤ አባባሉ እንዲወደድ ስልት ያለው የማለማመጃ ዘመቻ ወጣቱ ላይ እየተሰራ መሰለኝ። ዘይቤውን የሚናገሩት ብዙ የጥቁር ሀበሻ (ሀበ) ፈረንጃዊያን ብቅ ብለዋል። እነሱም ʻየአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስʼ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተውማንበብ ይቀጥሉ…