ቅድም ከምሽቱ 3ሰዓት ገደማ ሰፈሩ ድንገት በአንዲት ሴት እሪታ ተደበላለቀ። ከተቀመጥኩበት ብትት ብዬ ተነስቼ በመስኮት ወደ ውጭ ማተርኩ- አንዲት የተደናገጠች ሴት እጆቿን እያወራጨች ትተረማመሳለች… . ሌላዋ ሁለት እጆቿን ጭኖቿ መሃል ከታ አንዴ ጎንበስ አንዴ ቀና እያለች… ‘ደውሉ በናታችሁ! ስልክ ደውሉ!’ማንበብ ይቀጥሉ…
እያንዳንድሽ!
ወገን! ግጥሙ በሁዋላ ይደርሳል፤ ይሄ አጭር ማሳሰቢያ ነው! እያንዳንድሽ! ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ ፤ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በፀደይ ወቅት፤ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ ፤የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ፤አጎጠጎጤሽን በውሃ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፤ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ፤ በሽቦማንበብ ይቀጥሉ…
“ንግርት ያለኝ ሰባተኛ ንጉስ ነኝ”
ግርማዊነታቸው ዛሬ በረመዳን የመጀመሪያ ቀን የሳውዲ አቻቸውን (“አቻ” ሲባል ያው ሳውዲ በንጉስ የምትመራ ከመሆኗ አንጻር በቀጥታ ይወሰድልኝ) ሊያነጋግሩ በሳውዲ አረቢያ ተገኝተዋል።ትላንት በቲቪ እንዳየነው ንጉሰነገስቱ በግዛታቸው የሚያገለግሉ የተለያዩ ደጃዝማችና ራሶቻቸውን ሰብስብው ስለአገር አስተዳደር ሲያወጉ ሳት ብሏቸው ድሮ እቴጌ (እናታቸው) “የኢትዮጲያ 7ኛውማንበብ ይቀጥሉ…
እጅ በጆሮ
ማምሻውን ነው። ዝናብ ያረሰረሰውን የሰፈራችንን ኮብልስቶን መንገድ በጥንቃቄ እየረገጥኩ ወደ ቤቴ አዘግማለሁ። በድንጋዮቹ መሃከል የፈሰሰው ውሃ በረገጥኩት ቁጥር ፊጭ ፊጭ ይላል። ዘንቦ ማባራቱ ስለሆነ ይበርዳል። ፊጭ ፊጭ እያደረግኩ መራመዴን ስቀጥል፣ ከዚህ በፊት አይቼ በማላውቀው ሁኔታ በመንገዴ ላይ ከሰል አቀጣጥለው፣ በቆሎማንበብ ይቀጥሉ…
አብይ አህመድ (ዶክተር) በ “ፈርዖን” ፊት
ከአንድ ዓመት በፊት፣ ‹እርካብና መንበር› በሚል ርዕስ፣ ‹ዲራአዝ› በሚል ደራሲ ስም የወጣ መጽሐፍ ላይ እንዳነበብነው፣ መሪነት ድንገት ላያችን ላይ የምንጭነው አክሊል፣ ወይም እግረ መንገዳችንን እንደ ዘበት አንስተን የምናጠልቀው ቆብ መሆን የለበትም ።ስንመኘው፣ ስንጠብቀው፣ በትንሹ ስንለማመደው የነበረ፣ ለራሳችን የምናበረክተው፣ የምንፈተንበት፣ እኛንማንበብ ይቀጥሉ…
የኬዱክ እጆች
( ማሳጅ በባሊ፣ ኢንዶኖዢያ) -የቱሪስት ሃገር ስለሆነ ኑሮ እሳት ነው…እኔ ደግሞ ደሞዜ በጣም ትንሽ ነው። በወር ሁለት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ይከፍሉኛል ግን አይበቃኝም…የቤት ኪራይ ዘጠኝ መቶ ሺህ እከፍላለሁ… ኬዱክ ናት እንዲህ የምትለኝ። ኬዱክ በስመጥሩ ሆቴል ውስጥ ያለ ዝነኛ የስፓ አገልግሎትማንበብ ይቀጥሉ…
”የቱ ይበልጣል?“
ዛሬ ነው። የቀጠርኩት ሰው እስኪመጣ ፣ ከከተማችን ቅንጡ የገበያ ማዕከሎች በአንዱ ውስጥ ያለ ግብ እዞራለሁ። ለድሪቶነት ለሚቀርብ ሱሪ የሃምሳ ኪሎ ጤፍ ሂሳብ የሚያስከፍሉ ሞልቃቃ ቡቲኮች። ርካሹ ኬክ በ 40 ብር የሚሸጥባቸው ካፌዎች። አምስት ካሬ የማይሞላ የቄንጠኛ የግድግዳ ወረቀት ጥቅልን በሺህማንበብ ይቀጥሉ…
ከእንቅልፍ መልስ…
[ዳንሱን ከዳንሰኛው መነጠል ይቻላልን?] ___ ስለ ማንነት ሲነሳ በመስታወት ውስጥ ‘ፊቱን’ እያየ የሚመሰጥ ሰው ነው በዓይነ ሕሊናዬ የሚታየኝ… የናርሲስ ቢጤ … ናርሲስ በግሪክ ሚቲዮሎጂ ገጾች በውሃ ውስጥ የሚያየውን ምስል ለማምለክ ጥቂት የቀረው ሰው ሆኖ ተስሏል… በማንነት ጉዳይ ሁላችንም ናርሲስት ነን…ማንበብ ይቀጥሉ…
ባለ ከረሜላው ሰውዬ
ቢሮ ሆኜ ከስራ ፋታ ሳገኝ ማረፊያዬ ዩ ቲዩብ ነው። የድሮ ዘፈን እየጎረጎርኩ አዳምጣለሁ። ዛሬ ጠዋት የ80ዎቹ እና 90ዎቹን አር ኤንድ ቢ ሙዚቃዎች እየሰማሁ ሳለ የልጅነት አእምሮዬ ላይ ተነቅሶ ከቀረ አንድ ዘፈን ጋር ተገናኘን። ርእሱ ‹‹ካንዲ ሊከር›› ዘፋኙ ማርቪን ሴስ ይባላል።ማንበብ ይቀጥሉ…
“ይሸታታል”
ለምኖርበት ህንፃ የፅዳት ተጠሪ ስለሆንኩ በየወሩ እየዞርኩ ለሠራተኞች የሚከፈለውን ደሞዝ መዋጮ እሰበስባለሁ። ቅዳሜ እንደተለመደው እየዞርኩ የአንዷን ጎረቤቴን አፓርትማ አንኳኳሁ። ከፈተች። ከእሷ ቀድሞ ከቤቷ ውስጥ የወጣው ትኩስ እንጀራ ሸታ አወደኝ። የትኩስ እንጀራ ነገር አይሆንልኝም። ቁንጣን ይዞኝ ‹‹ማር እንኳን አልልስም›› ብዬማንበብ ይቀጥሉ…