“ሌ ሚዝረብል” እና “ዣንቫልዣ”

=== እንደ መግቢያ === እነሆ የቪክቶር ሁጎ ታላቅ ስራ የሆነውን “Les Misérables”ን ልንዘክረው ነው። ይህ ድርሰት የፈረንሳይ ምድር ካበቀለቻቸው የፈጠራ ስራዎች መካከል በጣም ዝነኛው ነው። መጽሐፉ በዓለም ዙሪያ የሚታወቀው “Les Miserables” (ሌ ሚዝረብል) በተሰኘው የፈረንሳይኛው ርዕስ ነው። በበርካታ ቋንቋዎች ሲተረጎምምማንበብ ይቀጥሉ…

ቀጠሮና እሷ

ዜጎቻችን ቀጠሮ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ቢደመር ለፍርድ ቀን፡ በዓለም የመጠናቀቂያ ዕለት የተከመረ ሐጢያት ሆኖ መንግስተ ሠማያት የሚባል ቦታ አንድ ሀበሻ አይገባም ነበር። መልካም ቀጠሮ አክባሪዎች በእግዜር ቀኝ ሲሰለፉ፤ 80ሚሊዮን የሚደርሰው ሀበሻ በጠቅላላ በእግዜር ግራ። ግራ ይግባንና። የማይገባኝ ግን ምክንያቱ ነው።ማንበብ ይቀጥሉ…

አስደሳች ጨዋታዎች

.(ከተስፋዬ ገብረአብ ) ተስፋዬ ገብረ-አብ “በጋዜጠኛው ማስታወሻ” በርካታ ፖለቲካ-ነክ ወጎችን አውግቶናል። እኔ እዚህ የምጽፍላችሁ ግን ፖለቲካውን ሳይሆን ተደጋግመው ቢነገሩ የማይሰለቹ ሌሎች ጨዋታዎቹን ነው። (እኒህን ጨዋታዎች የቀዳሁት ከዚያው መጽሐፍ ነው)። ===አቶ ፍሬው ለምለም እና የቼክ እደላው=== አቶ ፍሬው ለምለም ደግ አዛውንትማንበብ ይቀጥሉ…

ጅምጃሚዎች

(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) ላሎ ወደ መርሀባ ተጠጋና ምንጣፉ ላይ በጀርባዋ አንጋለላት። ከዚያ በእግሮቿ ማሃል በርከክ አለና ቁልቁል ተመለከታት። ፊቷ በላብ ተጠምቋል!! ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። እግሯን ብድግ አድርጎ ወደ ደረቱ ሳበው። አንባቢ ሆይ! የወሲብ ታሪክ የምተርክልህ መስሎህ እግርህን በእግርህ ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቂት ስለ “አዳል”

በመካከለኛው የታሪክ ዘመን (Medieval Era) ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን፣ ሶማሊላንድን እና ሶማሊያን በሚያቅፈው የአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና የተለያየ ቅርጽና አወቃቀር የነበራቸው መንግሥታት ተመሥርተዋል። ከነዚያ መንግሥታት መካከል ከአስር የማያንሱት የሙስሊም ሱልጣኔቶች ነበሩ። ከሱልጣኔቶቹ መካከል ስሙ በጣም ገንኖ የነበረውና በአፍሪቃ ቀንድ ሕዝቦች ታሪክ፣ ጂኦ-ፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…

እኛ፣ሾፌሩና አውቶብሱ

‹ዛጎል› ልቦለድ ውስጥ የምናገኘው ዮናስ የተባለው ገጸ ባሕርይ እንደሚከተለው ያስባል፤ያምናል፤ይናገራልም! ‘በእኛ ፈቃድ አይደለም ነገሮች የሚከወኑት። እግዜራችን ነው ሾፌር። እሱ ነው ፈላጭ ቆራጭ! እሱ ነው የእኛ ሃይል። በየትኛው ጊዜ – በየትኛው ቦታ – እኛን ከመኪናው ማውረድ እንዳለበት የሚወስን። እኛ ‘ወራጅ አለ’ማንበብ ይቀጥሉ…

በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3

ውድ አንባብያን! <ያልተቀበልናቸው>የተሰኘው አዲሱ መጽሐፌን በየመጻሕፍት መደብሩና በየአዙዋሪዎቹ እጅ ታገኙታላችሁ።መጽሐፉ በእጃችሁ እስኪገባ፣አሁንም አንድ ቁንጽል ጻሪክ ከመሐፉ ልጋብዛችሁ።  በውበት ሳሎኑ ውስጥ – 3 ——- የተቀመጥኩት መግቢያው በር አጠገብ ነበር። የሆነ ሰው፣ እጀርባዬ እንደቆመ ትከሻዬ ነግሮኝ ቀና አልኩ። ቀና ስል፣ ከዚህ ቀደምማንበብ ይቀጥሉ…

ባይተዋሩ ግመል

አንዳንድ ድምጻውያን አዲስ አልበም ሊያወጡ ሲሉ ነጠላ ዜማቸውን ቀደም ብለው እንደሚለቁት፣ከአዲሱ ‹ያልተቀበልናቸው› ከተሰኘው መጽሐፌ ከአንዱ ወግ ቀንጭቤ ጀባ ልላችሁ ወደድኩ።  ባይተዋሩ ግመል (….) ግመሉ የተገለለ ነው – ከወንዙ ተነጥሎ፣ ከወገኑ ተለይቶ፣ ለተሻለ ኑሮ፣ ወይም ለተሻለ የመንፈስ ፀጥታ፣ ወይም ለተሻለ ዕውቀትማንበብ ይቀጥሉ…