ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሁለት)

ከእኔ በፊት ሁለት ሚስት አግብቶ እንደነበር ሳላውቅ አይደለም ያገባሁት። አውቅ ነበር። ለሁለቱም ሚስቶቹ ልክ ከእኔ ጋር እንዳደረገው የሀብት ውርስ ኮንትራት አስፈርሟቸው እንደነበርም አልደበቀኝም ነበር። በፍቅሩ ነሁልዬ ከእኔ በፊት የነበረው ህይወቱ ገሀነም እሳት ጭስ ሳይሸተኝ ቀርቶም አይደለም። ወይም ፍቅሬ አቅሉን አስቶትማንበብ ይቀጥሉ…

እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!

ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)

«ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?»ማንበብ ይቀጥሉ…

የተሳሳተ

ከምኡዝ ጋራ ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ተገናኘን፥ “ ከመንገድ ዳር ካለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን አቧራና ቡና እየጠጣን አላፊ አግዳሚውን እያየን እናወራለን፥ ድንገት አንዲት ሴት ብቅ አለችና ወደ ምኡዝ እያየች “ አንተ አለህ?” ብላ ባድናቆት ጮኸች፤ ሁለት እጆቿን በሰፊውማንበብ ይቀጥሉ…

ከአበታር ወደ አባተ

አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮችማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቆማ

ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል። ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም። ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤ አሁን በመንሽማንበብ ይቀጥሉ…

ጥቆማ

ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው ፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል፥ ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም፥ ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤( አሁንማንበብ ይቀጥሉ…

እንደምትወዳት ንገራት

ሕይወት የብድር በሬ፥ መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል። ቀለበት፥ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም ቀናት ሳምንታት ወራት ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያጸድ በሮችማንበብ ይቀጥሉ…

ግ-ሽበት

አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ማንበብ ይቀጥሉ…

“መዶሻህን ብላው”

ወዳጄ (Netsanet) እንደነገረኝ ሰውዬው እሁድ ቀን እቤቱ ጋደም ብድግ ሲል ይቆይና ግድግዳው ላይ የተነቀለች ሚስማር አይቶ ሊመታት ቢፈልግ መዶሻ ያጣል። ጎረቤቱን ሊጠይቀው በሩጋ ከደረሰ በኋላ «ተኝቶ ቢሆንስ» ብሎ ይመለሳል። እቤቱ ከመድረሱ በፊት ግን «እህ የተኛ እንደሆነስ? መዶሻውን ከሰጠኝ በኋላ ተመልሶማንበብ ይቀጥሉ…