‹‹ከደነዘዘ ሃብታም ከመወለድ ነቃ ካለ ድሃ ቤተሰብ መውጣት በስንት ጠዓሙ ›› አለች ልእልት ታሪኳን ስትጀምርልኝ …. እኔ እንኳን ‹‹ገንዘብ የደነዘዘውን ሁሉ ነቃ የሚያደርግ አስማት ነገር›› እንደሆነ እየሰማሁ ስላደኩ አባባሏ ብሶት የወለደው የተሳሳተ ጥቅስ መስሎኝ ነበር …. እውነቴን ነው ‹‹እከሊት ብርማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል (ክፍል ስድስት)
ዛሬ በጧቱ አንድ ጅንስ ሱሪና ነጭ አዲዳስ ሲኒከር ጫማ ያደረገ (እድሜው አምሳ የሚሆን እንቢ አላረጅም ነገር) ማስቲካ የሚያላምጥ ….ደግሞ በሽቶ ተጠምቆ የወጣ የሚመስል ….(ልክ ሲገባ ክፍሉ በሽቶ ተሞላ) ወደተኛሁባት ክፍል ገባና መነፅሩን አውልቆ አንዴ ክፍሏን በትእቢተኛ አይኑ ገርምሟት ሲያበቃ …ወደእኔማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል (ክፍል አምስት)
እኔማ ችግር አለብኝ …ከምር ችግር አለብኝ !! አሁን ሰው ሲሉኝ አሁን አፈር …አሁን ደህና ነገር እያወራሁ በቃ ሰው አፉን ከፍቶ እየሰማኝ በመሃል ዘብረቅ አድርጌ ሰው ማስቀየም ! ኤጭ …..ይሄ ልክፍት ነው እንጅ ሌላ ምን ይባላል … ለኔማ እንኳን ቢላ ጎራዴምማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል (ክፍል አራት )
አንዲት መልከመልካም ነርስ ነበረች እየተመላለሰች የምትንከባከበኝ … ከስራዋ በተጨማሪ በመጣች ቁጥር የምታገኛቸው ወጣት ጓደኞቸ ጋር አንድ ሁለት ቃላት (አለ አይደል እንደማሽኮርመም የሚያደርጉ) ስለምትወራወር የእኔን ክፍል ከስራ ቦታነት በተጨማሪ እንደመዝናኛ ቦታ ሳታያት አልቀረችም … ታዲያ ይች ነርስ እናቴም ጋር ከመግባባቷ ብዛትማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል (ክፍል ሦስት)
‹‹ተመስገን…. ዋናው መትረፉ ነው ! ወደልቡ ከፍ ቢል ኖሮ ወይ ቆሽቱን ቢያገኘው የማን ያለህ ይባላል ›› የሚል ድምፅ ስሰማ ልክ እንደብርቱ ክንድ ትከሻና ትከሻየን ይዞ እያርገፈገፈ ከከባድ እንቅልፍ የቀሰቀሰኝ መሰለኝ ! አ?? አላመንኩም …. መትረፌ ብቻ አይደለም የገረመኝ …. የመትረፌንማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል! (ክፍል ሁለት)
የተጣሉ ባልና ሚስትን ለማስታረቅ ከሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነገሮች መካከል አንዱ የተጣሉበትን ምክንያት ጠንቅቆ ማወቅና …የፀቡን ምክንያት ወይ ((ማካበድ)) ወይ ((ማቃለል)) ነው ….ለምሳሌ የፀቡ ምክንያት ባል ሚስቱን ‹‹ ከጎረቤቷ የሚገኝ ጎረምሳ ጋር አጓጉል ነገር ጀምራለች ›› በሚል ‹ተልካሻ ምክንያት› ጠርጥሯት ቢሆንናማንበብ ይቀጥሉ…
በአልጋው ትክክል! (ክፍል አንድ)
በዛ ….ከምር በዛ …!! እንዴ እግዜር በሚያውቀው እኔ ክፉ ነገር አስቤ ወይ የሱን ትዳር ለመበተን አስቤ ያደረኩት ነገር አይደለም ….በቃ በበጎነት በፍፁም ቅንነት ያደረኩት ነገር ነው ! እውነቴን ነው …የሱ ትዳር ስለተበተነ እኔ ምን አገኛለሁ ?…ትዳሩስ ስለሞቀና ስለደመቀ ምን አጣለሁማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹አላውቅም›› ማለት ነውር የሆነበት አገር እየገነባን ነው ?
አገራችን ላይ ትልቁ ችግር የሚመስለኝ ….ታላላቆች በሁሉም ነገር ትልቅ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብና ‹ታናናሾች › በሁሉም ነገር ትንሽ እንደሆኑ አድርጎ ማናናቅ ነው …ለምሳሌ ሰፈራችን ውስጥ ያለን ታዋቂ አርቲስት …ህግም ፣ፍልስፍናም፣ መሃንዲስነትም ፣ የተበላሸ ቧንቧ ጥገናም ፣ ፖለቲካም ፣ስፖርትም ከሱ በላይ አዋቂማንበብ ይቀጥሉ…
እልፍ አእላፍ እኛ!
ቅዳሴው ሰማዩን ሰንጥቆት አረገ …. በደስታው ከበሮ ልብ አረገረገ መሬት አደይ ሞላች ውሽንፍሩ አባራ የቢራቢሮ አክናፍ እልፍ ቀለም ዘራ የፀሃይ ብርሃን በመንደሩ በራ….. እንዲህ ከጎረቤት እልልታ ያጀበው የዶሮ ወጥ ሽታ የነጭ ልብስ ወጋገን የሰዎች ቱማታ እንዲህ ወደማጀት የተከፋች እናት አይኗማንበብ ይቀጥሉ…
መጥተናል መጥተናል…. ቀጠሮ አክብረናል!
የቡሄ ጭፈራ እጅግ በጣም ‹‹አስገራሚ ››ከሚሆንባቸው ቦታወች አንዱ ኮንዶሚኒየም ህንፃወች ላይ ይመስለኛል !! ህፃናቱ በዱላወቻቸው አራተኛ ፎቅ ላይ ወለሉን እየደቁ ሲጨፍሩ ..ጠቅላላ ብሎኩ ይነቃነቃል ይንጋጋል …ህንፃው ከቆርቆሮ የተሰራ ነው የሚመስላችሁ ! በዛ ላይ ሰወች ኮንዶሚኒየም ቤት ሲኖሩ ከኢትዮጲያ ውጭ (ኧረማንበብ ይቀጥሉ…