የታፈኑ ጥያቄዎች እና ፍላጎቶች ተብላልተው ጉልበት ሆነው ይመጣሉ እንጂ ተዳፍነው አይቀሩም! የብሔር ጥያቄም እንዲያው ነው። ከዘመነ ኃይለስላሴ በፊት ግዛቶች ራሳቸው በራሳቸው የማስተዳደር አንፃራዊ ነፃነት ነበራቸው።የሚያስተዳድራቸው የራሳቸው ሰው ነበር። ልዝብ ፌደራሊዝም አይነት ነበሩ። ኃይለስላሴ መጥተው ያንን ሰባበሩት። (ዶ/ር ፍስሃ አስፋው እናማንበብ ይቀጥሉ…
ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሥልጣን
ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በፈቃዱ ከባለሥልጣንነት ተሰናበተ፤ ብዙ ሰዎች አስተ አስተያየታቸውን በቴሌቪዥን ሲገልጹ እንደሰማሁት ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በፈቃዱ ለመሰናበት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ይላሉ፤ ይህ የማስታወስ ችሎታችንን ዝቅተኛነትን ያመለክታል፤ ጸሐፌ ትእዘዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድን ረስተናል! (ስለዚህ ጉዳይ በእንዘጭ! እምቦጭ! የኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ዘርዘርማንበብ ይቀጥሉ…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስመልከት ስለፍቅር እንሰብካለን
በፊት … ስለፍቅር ሳላነብ በፊት… ፍቅር በሶስት ይከፈላል ብዬ አስብ ነበር። ሰዎች… ነገ ምን እንደሚፈጠር ሳናውቅ ማውራት የምንችለው ስለምን እንደሆነ የማናውቅ ፍጡራን መሆናችንን ማመን ታላቅ ጥበብ እንደሆነ የገባኝ ግን ዘግይቶ ነው። በዘገይም አብሮ የገባኝ እውነት ምስክር መሆኔን አውጃለሁ። ይህንን አምኜምማንበብ ይቀጥሉ…
የካቲት እና ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የካቲት ታሪካዊ ወር ነው። ታላላቅ አብዮቶችም ታላላቅ ድሎችም በየካቲት ወር ተከናውነዋል። ዐድዋን ያህል ከፍታው ሰማየ ሰማያትን የሚነካ ድል የተገኘው በየካቲት 23 ነው። ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችን (የአዲስ አበባ ኗሪዎች ብቻ) በፋሽስት በግፍ የተጨፈጨፉትም በየካቲት 12 ነው። የካቲትማንበብ ይቀጥሉ…
ባሩድ እና ብርጉድ
ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?
የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም። በአንድ በኩል ‹ጸረ መንግሥት ዝማሬ ያሰሙ ነበር›፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹ድንጋይ ይወረውሩ ነበር› የሚሉት ምክንያቶች የጸጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ጥይት እንዲተኩሱ የሚያበቁ ሕጋዊና ሞራላዊ ምክንያቶች አይደሉም። ማንኛውምማንበብ ይቀጥሉ…
ከያስተሰርያል በላይ እንደሚወደን አሳይቶናል
The other side of Teddy Afro >Leadership Quality ….ከያስተሰርያል በላይ እንደሚወደን አሳይቶናል #ባህር_ዳር የዛሬ አራት አመት አዲስ አበባ ላይ እንዲህ ብሎን ነበር ቴዲ:- #ግዮን_ሆቴል ህዝብ ያስተሰርያል እንዲዘፈን የነበረውን ጉጉት አይቶ ቴዲ እንዲህ ብሎ ጠይቆ ነበር “ያስተሰርያል ስድብ ነው እንዴ ? ” ቴዲማንበብ ይቀጥሉ…
ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር!
/የታሪካዊው ሙዚቃ ድግስ ወፍ በረር ቅኝት/ እጅግ ከበዙ ተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ በማስታዋቂያ ብቻ ተገድቦ ያልቀረው ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር የተሰኘው የብላቴናው የሙዚቃ ኮንሰርት ወደ እውነትነት ተቀይሮ በስኬት ተጀምሮ በስኬት ተጠናቋል።የኮንሰርቱ አዘጋጆች /በተለይም ቴዲ አፍሮ/ ከሙዚቃ ኮንሰርቱ አንድ ቀን ቀደም ሲል በወልድያማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ነገ ዛሬ ይሆን››
እንግዲህ ጅማሬው ከሆነ ከአንጀታችሁ ‹‹እናዳምጣለን….ንገሩን›› ካላችሁ… የይስሙላ፣ የእድሜ ማራዘሚያ፣ የጥገና እና ተንፏቃቂ ለውጥ አንፈልግም። ጉልቻው እንዲቀያየር፣ ሽንቁር የበዛበት ግድግዳ ቀለም ፣ አሳማው ሊፕሰቲክ እንዲቀባ አንሻም። ባረጀ እና ያፈጀው ‹‹ተሃድሶ›› ሀረግ ዳግም መደለል፣ ዳግም መታለል አንፈልግም። የ‹‹ተጨፈኑ ላሞኛችሁ›› ፖለቲካ አንገሽግሾናል። የዘመናት‹‹እድሳትማንበብ ይቀጥሉ…