ቴዲ አፍሮ ‹‹ቀና በል›› የሚለውን ሙዚቃውን በለቀቀ ማግስት ለስራ ጉዳይ ጎረቤት ሃገር ተላክሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ሆቴሌ የሚወስደኝ ታክሲ ውስጥ ገብቼ ብዙዎችን ያላቀሰውን ሙዚቃ በጥሞና ለማዳመጥ የጆሮ ማዳመጫዬን ከስልኬ አገናኘሁ። ልክ ቴዲ ‹‹አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ-ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ›› ብሎ መዝፈን ሲጀመርማንበብ ይቀጥሉ…
ስለአወዳመት
አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ማንበብ ይቀጥሉ…
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ
እዚሁ አዳራሽ ውስጥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የአገር ባህል ልብስ ለብሰው በአንጋፋው ሱዳናዊ ዘፋኝ መሃመድ ዋርዲ ዘፈን ከመላው ህዝብ ጋር ጨፈሩ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ…የትግል አጋራቸው የአገር መከላከያ ሰራዊትኢታማዦር ሹም ሳእረ መኮነን አስከሬን በእንባ ተሸኘ። እዚሁ አዳራሽ ውስጥ …እነኦነግና ግንቦት ሰባት አገርማንበብ ይቀጥሉ…
እያረምን ወይስ እያበድን እንሂድ
ገበሬው ለሙግት ወደ ሸንጎ ሄዶ ሲመጣ የገዛ ወዳጆቹ የዘራውን እህል ሳያርሙ፣ ሳይኮተኩቱ ጠበቁት። ማሳውን እያየ ያብዳል። እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? ይህን ያደረጉት እነ እንቶኔ ናቸው? ይህን ያደረጉት እኔን ሊጎዱ ነው? ድሮም እነርሱ አይወዱኝም ነበር፤ በቃ የሰው ነገር መጨረሻው እንደዚህ ሆነ ማለትማንበብ ይቀጥሉ…
እርግብ እና ዋኔ
“ውጪ…ልን!”
የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ነበር የተማሪዎቼ የንድፍ ስራ በሙሉ አረንጓዴ…ቢጫ…ቀይ መሆን የጀመረው። የሆነ የቪላ ንድፍ ከመስራታቸው በፊት ሀሳባቸውን በቅርፃ ቅርፅ እንዲያስረዱ ቀለል ያለ ስራ እንሰጣቸዋለን። ያው ያኔ የነበረው መንፈስ ከእጩ አርክቴክትነታቸው በልጦባቸው ቢሮ ውስጥ የሚከመረው ነገር በሙሉ አንድ አይነት ሆኖማንበብ ይቀጥሉ…
ክትባት እንዴት እንዳመለጠኝ
አበሻ ገራሚ ህብረተሰብ ነው! ማስክ ገድግደህ ሲያይህ” ይሄን ያህል ትንቦቀቦቃለህ እንዴ” እያለ ያሸማቅቅሀል ፤ ከዚያ አጅሬው አስተኝቶ ለሳምንታት ያክል አበራይቶ ትቶት ይሄዳል፤ ከዚያ እንዴት ነህ? ስትለው” በዝሆን እግሩ ረግጦ አድቅቆ ለቀቀኝ በማለት ፈንታ” ይዞ ለቀቀኝ “ በማለት አቃሎ ይነግርሃል፤ ከህመሙማንበብ ይቀጥሉ…
አሜሪካን ፀሀይና የአገሬን ሚድያ ያመነ
“ስሙኝ ልንገራችሁ ታሪኬን ባጭሩ” አለ አለማየሁ እሼቴ የሆነ ጊዜ ! ከዛ ረዘም አድርጎ ዘፈነ። ስሙኝ ! ትናንት በቤቴ መስኮት መስታወት አሻግሬ ወደ ውጭ ስመለከተ ፀሀይ በሰላሳ ጥሩሷ ፉዋ ብላለች! እሰይ ! Thank you Global warming አልኩ! ወደ ባህር ዳርቻው ወጣማንበብ ይቀጥሉ…
ድንጋይ ዳቦ ሆነ
አንዲት አረጋዊት ጥቁር ኢትዮጵያዊት ትመካበት የላት ባለፀጋ ዘመድ ፊቷ የለበሰ፤- ፅናት ላብና አመድ እሷ አለቃ ሆና፤ ክንዶቿን ቀጣሪ እሱዋ ድሃ ሆና ፤ የሀብታሞች ጧሪ:: እየተጋች አድራ እየለፋች ስትውል እድሜና ተስፋዋን፤ ያስተሳሰረው ውል ቢቀጥን ቢሳሳ ከሸረሪት ፈትል መሀረብ ዘርግታ ተዘከሩኝ ሳትልማንበብ ይቀጥሉ…
አይ የሰው ኑሮ መለያየት!
ካናዳ የሚገኘው የመስሪያ ቤታችን ቅርንጫፍ ባልደረባ ለስራ ጉዳይ የኢሜል መልእክት ልካልኝ ምን ብላ ጀመረች? ‹‹እንዴት ይዞሻል? አዲስ አበባ ያላችሁ ሰራተኞች ከቻላቸሁ ከቤት እንድትሰሩ እንደተመከራችሁ ሰማሁ። እኛ ያው በግድ፣ በመንግስት ትእዛዝ ቤት ታሽገን ተቀምጠን ልናብድ ነው። ወላ ሬስቶራንት ሄዶ መብላት የለ፣ማንበብ ይቀጥሉ…